Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነርሱም መልሰው፦ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም፦ ኤልያስ፥ ሌሎችም፦ ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል ይላሉ አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነርሱም፣ “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ከቀድሞ ነቢያት አንዱ ከሙታን ተነሥቷል ይላሉ” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነርሱም መልሰው፦ “ ‘መጥምቁ ዮሐንስ፥’ ሌሎችም ‘ኤልያስ፥’ ሌሎችም ‘ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል፤’ ይላሉ፤” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እነርሱም “አንዳንዶች ‘አጥማቂው ዮሐንስ ነው፤’ ሌሎች ‘ኤልያስ ነው፤’ ይሉሃል፤ ‘ከቀድሞዎቹ ነቢያት አንዱ ከሞት ተነሥቶአል፥’ የሚሉም አሉ፤” ብለው መለሱለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ነው የሚ​ሉህ አሉ፤ ኤል​ያስ ነው የሚ​ሉ​ህም አሉ፤ ከቀ​ደ​ሙት ነቢ​ያት አንዱ ተነ​ሥ​ቶ​አል የሚ​ሉ​ህም አሉ” አሉት።

参见章节 复制




ሉቃስ 9:19
12 交叉引用  

እነሆ፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።


ለሎሌዎቹም፦ ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው፤ እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል፥ ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል አለ።


በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።


ስሙም ተገልጦአልና ንጉሡ ሄሮድስ በሰማ ጊዜ፦ መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል አለ።


ሌሎችም፦ ኤልያስ ነው አሉ፤ ሌሎችም፦ ከነቢያት እንደ አንዱ ነቢይ ነው አሉ።


ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፦ ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው።


እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ አለ።


እንኪያስ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን? ብለው ጠየቁት። አይደለሁም አለ። ነቢዩ ነህን? አይደለሁም ብሎ መለሰ።


ስለዚህ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎች ይህን ቃል ሲሰሙ፦ “ይህ በእውነት ነቢዩ ነው” አሉ፤


በመካከላቸውም መለያየት ሆነ። ከዚህም የተነሣ ዕውሩን፦ “አንተ ዓይኖችህን ስለ ከፈተ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ደግሞ አሉት። እርሱም፦ “ነቢይ ነው” አለ።


跟着我们:

广告


广告