Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 9:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ቀኑም ይመሽ ጀመር፤ አሥራ ሁለቱም ቀርበው፦ በዚህ በምድረ በዳ ነንና በዙሪያችን ወዳሉ መንደሮችና ገጠሮች ሄደው እንዲያድሩና ምግብ እንዲያገኙ ሕዝቡን አሰናብት አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ቀኑም ሊመሽ ሲል፣ ዐሥራ ሁለቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ያለነው በምድረ በዳ ስለ ሆነ፣ ሕዝቡ ወደ አካባቢው መንደርና ገጠር ሄደው ማደሪያና ምግብ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ቀኑም ይመሽ ጀመር፤ ዐሥራ ሁለቱም ቀርበው፦ “በዚህ በምድረ በዳ ስላለን በዙሪያችን ወዳሉ መንደሮችና ገጠሮች ሄደው እንዲያድሩና ምግብ እንዲያገኙ ሕዝቡን አሰናብት፤” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ቀኑ ሊመሽ ሲል፥ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “ይህ ያለንበት ቦታ በረሓ ነው፤ ስለዚህ ሰዎቹ በአካባቢው ወዳሉት ከተሞችና ገጠሮች ሄደው ምግብና ማደሪያ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው፤” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ቀኑም በመሸ ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት መጥ​ተው፥ “ያለ​ን​በት ምድረ በዳ ነውና በዙ​ሪ​ያ​ችን ወዳሉ መን​ደ​ሮ​ችና ገጠ​ሮች ሄደው እን​ዲ​ያ​ድሩ የሚ​በ​ሉ​ት​ንም እን​ዲ​ያ​ገኙ ሕዝ​ቡን አሰ​ና​ብት” አሉት።

参见章节 复制




ሉቃስ 9:12
13 交叉引用  

የሰላምን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እገባለሁ ክፉዎችንም አራዊት ከምድር አጠፋለሁ፥ ተዘልለውም በምድረ በዳ ይኖራሉ በዱርም ውስጥ ይተኛሉ።


በምድረ በዳ፥ እጅግ በደረቀ ምድር አውቄህ ነበር።


ኢየሱስም በሰማ ጊዜ ከዚያ ብቻውን ወደ ምድረ በዳ በታንኳ ፈቀቅ አለ፤ ሕዝቡም ሰምተው ከከተማዎቹ በእግር ተከተሉት።


እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት እያሉ ለመኑት።


ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ፦ ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለ ሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤ በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም አላቸው።


ሕዝቡም አውቀው ተከተሉት፤ ተቀብሎአቸውም ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ይነግራቸው ነበር፥ መፈወስ ያስፈለጋቸውንም ፈወሳቸው።


እርሱ ግን፦ እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው አላቸው። እነርሱም፦ ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን፥ ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ የሚበልጥ የለንም አሉት፤


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፤ እርሱም የጥብርያዶስ ባሕር ነው።


ወደ ፊትም ደግሞ ደስ ይለኛል ይህ በጸሎታችሁና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ መሰጠት ለመዳኔ እንዲሆንልኝ አውቃለሁና፥


跟着我们:

广告


广告