Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 7:44 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፤ “ይህችን ሴት ታያታለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ አንተ ለእግሮቼ ውሃ እንኳ አላቀረብህልኝም፤ እርሷ ግን እግሮቼን በእንባዋ እያራሰች በጠጕሯ አበሰች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርሷ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች፤ በጠጉርዋም አበሰች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ሴትዮዋ መለስ ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ስገባ አንተ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብክልኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን በእንባዋ አጥባ በጠጒርዋ አበሰችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ወደ ሴቲ​ቱም ዘወር ብሎ ስም​ዖ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ይህ​ቺን ሴት ታያ​ታ​ለ​ህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእ​ግ​ሮች ውኃ ስንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን አል​ቅሳ በእ​ን​ባዋ እግ​ሬን አራ​ሰች፤ በጠ​ጕ​ር​ዋም አበ​ሰች።

参见章节 复制




ሉቃስ 7:44
11 交叉引用  

ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፤


ጌቶቼ ሆይ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ ከዚያም እደሩ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁም ትሄዳላችሁ። እነርሱም፤ በአደባባዩ እናድራለን እንጂ አይሆንም አሉት።


ስምዖንም አወጣላቸው። ሰውዮውም እነዚያን ስዎች ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባቸው ውኃ አመጣላቸው እግራቸውንም ታጠቡ ለአህዮቻቸው አበቅ ስጣቸው።


ዳዊትም ኦርዮን፦ ወደ ቤትህ ሂድ፥ እግርህንም ታጠብ አለው። ኦርዮም ከንጉሡ ቤት ሲወጣ ማለፊያ የንጉሥ መብል ተከትሎት ሄደ።


በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች።


ስምዖንም መልሶ፦ ብዙ የተወለቱ ይመስለኛል አለ። እርሱም፦ በእውነት ፈረድህ አለው።


በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።


ልጆችን በማሳደግ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።


እናንተ ግን ድሆችን አዋረዳችሁ። ባለ ጠጎቹ የሚያስጨንቁአችሁ አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤትም የሚጎትቱአችሁ እነርሱ አይደሉምን?


ወደ ቤቱም አስገባው፥ ለአህዮቹም ገፈራ ጣለላቸው፥ እግራቸውንም ታጠቡ፥ በሉም ጠጡም።


ተነሥታም በግምባርዋ ወድቃ እጅ ነሣችና፦ እነሆ፥ እኔ ገረድህ የጌታዬን ሎሌዎች እግር አጥብ ዘንድ አገልጋይ ነኝ አለች።


跟着我们:

广告


广告