Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 7:40 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ኢየሱስም መልሶ፦ ስምዖን ሆይ፥ የምነግርህ ነገር አለኝ አለው። እርሱም፦ መምህር ሆይ፥ ተናገር አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ኢየሱስም፣ “ስምዖን ሆይ፤ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። እርሱም፣ “መምህር ሆይ፤ ንገረኝ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ኢየሱስም መልሶ፦ “ስምዖን ሆይ! አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ፤” አለው። እርሱም፦ “መምህር ሆይ! ተናገር፤” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ኢየሱስም፦ “ስምዖን ሆይ፥ አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ፤” አለው። እርሱም፦ “መምህር ሆይ! እሺ ንገረኝ!” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ስም​ዖን ሆይ፥ የም​ነ​ግ​ርህ ነገር አለኝ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ተና​ገር” አለው።

参见章节 复制




ሉቃስ 7:40
16 交叉引用  

እርሱም “በሰላም ነው፤” አለ። ደግሞም “ከአንቺ ጋር ጉዳይ አለኝ፤” አለ፤ እርስዋም “ተናገር፤” አለች።


ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም፥ በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ስስታቸውን ትከተላለች።


እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።


ወዲያውም ወደ ኢየሱስ ቀረበና፦ መምህር ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን ብሎ ሳመው።


በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።


ከአለቆችም አንዱ፦ ቸር መምህር፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።


ኢየሱስም አሳባቸውን እያወቀ መልሶ፦ በልባችሁ ምን ታስባላችሁ?


ኢየሱስም መልሶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤


እርሱ ግን አሳባቸውን አውቆ እጁ የሰለለችውን ሰው፦ ተነሣና በመካከል ቁም አለው፤ ተነሥቶም ቆመ።


የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ በልቡ አሰበ።


ለአንድ አበዳሪ ሁለት ተበዳሪዎች ነበሩት በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት በሁለተኛውም አምሳ።


እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።


ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ወደዱ አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁ ስላልሁ፥ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን?


ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን” አሉት።


መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለም መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።


跟着我们:

广告


广告