Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 18:43 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 በዚያን ጊዜም አየ፥ እግዚአብሔንም እያከበረ ተከተለው። ሕዝቡም ሁሉ አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ሰውየውም ወዲያውኑ ማየት ቻለ፤ እግዚአብሔርንም እያከበረ ኢየሱስን ተከተለው። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያዩ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 በዚያን ጊዜም አየ፤ እግዚአብሔርንም እያወደሰ ተከተለው። ሕዝቡም ሁሉ ይህን አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ዐይነ ስውሩም ወዲያውኑ ማየት ቻለ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ኢየሱስን መከተል ጀመረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 በዚ​ያን ጊዜም አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ተከ​ተ​ለ​ውም፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ኑት።

参见章节 复制




ሉቃስ 18:43
30 交叉引用  

በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን የገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል።


ዕውሮችንም በማያቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፥ በማያቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፥ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፥ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውምም።


ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ


በመቅደስም ዕውሮችና አንካሶች ወደ እርሱ ቀረቡና ፈወሳቸው።


ሕዝቡም አይተው ተደነቁ፥ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ እግዚአብሔርን አከበሩ።


ይህንም ሲናገር ሳለ የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ሁሉ ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው።


ወደ ደብረ ዘይት ቍልቍለትም አሁን በቀረበ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ሁላቸው ደስ እያላቸው ተአምራትን ሁሉ ስላዩ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ጀምረው፦


በአጠገብዋም ቆሞ ንዳዱን ገሠጸውና ለቀቃት፤ ያንጊዜውንም ተነሥታ አገለገለቻቸው።


ሁሉንም መገረም ያዛቸው፥ እግዚአብሔርንም አመስግነው፦ ዛሬስ ድንቅ ነገር አየን እያሉ ፍርሃት ሞላባቸው።


ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ ተገረሙ። ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ሁሉ ሲደነቁ፥


ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦ “እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው” እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።


እነርሱም እንደ ምን እንደሚቀጡ ምክንያት ስላላገኙባቸው፥ እንደ ገና ዝተው ከሕዝቡ የተነሣ ፈቱአቸው፤ ሰዎች ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበርና።


ስለ እኔም እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበር።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


跟着我们:

广告


广告