Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 15:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፥ ከዚያም እያባከነ ገዘቡን በተነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ብዙም ቀን ሳይቈይ፣ ታናሹ ልጅ ድርሻውን ሁሉ ጠቅልሎ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፤ በዚያም በማጋጣነት ንብረቱን አባከነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፤ ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከጥቂት ቀን በኋላ ታናሽዮው ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፤ በዚያም አገር ገንዘቡን ሁሉ በከንቱ አባከነ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ያ ትንሹ ልጁ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ በዚ​ያም በመ​ዳ​ራት እየ​ኖረ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ በተነ፤ አጠ​ፋም።

参见章节 复制




ሉቃስ 15:13
35 交叉引用  

ኃጢአተኛ ወገንና በደል የተሞላበት ሕዝብ፥ የክፉዎች ዘር፥ ርኵሰትን የምታደርጉ ልጆች ሆይ፥ ወዮላችሁ! እግዚአብሔርን ትተዋል የእስራኤልንም ቅዱስ አቃልለዋል ወደ ኋላቸውም እየሄዱ ተለይተዋል።


እነሆም፥ ሐሤትና ደስታ በሬንና በጉንም ማረድ ሥጋንም መብላት የወይን ጠጅንም መጠጣት ሆነዋል፥ እናንተ፦ ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ ብላችኋል።


ከመንገድ ፈቀቅ በሉ፥ ከጐዳናውም ዘወር በሉ፥ የእስራኤልንም ቅዱስ ከእኛ ዘንድ አስወግዱ ይሉአቸዋል።


ኑ የወይን ጠጅ እንውሰድ፥ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፥ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፥ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል ይላሉ።


ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋልና፥ እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል፥ የተቀደዱትንም ጕድጓዶች፥ ውኃውን ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጕድጓዶች፥ ለራሳቸው ቆፍረዋል።


ትውልድ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ተመልከቱ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንሁባትን? ሕዝቤስ ስለ ምን፦ እኛ ፈርጥጠናል፥ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል?


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከንቱነትንም የተከተሉ፥ ከንቱም የሆኑ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው?


ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አድርጌለሁ? በምንስ አድክሜሃለሁ? መስክርብኝ።


ከእነርሱም ታናሹ አባቱን፦ አባቴ ሆይ፥ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው።


ሁሉንም ከከሰረ በኋላ በዚያች አገር ጽኑ ራብ ሆነ፥ እርሱም ይጨነቅ ጀመር።


ነገር ግን ገንዘብህን ከጋለሞቶች ጋር በልቶ ይህ ልጅህ በመጣ ጊዜ፥ የሰባውን ፊሪዳ አረድህለት አለው።


ደግሞም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ መጋቢ የነበረው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ በእርሱ ዘንድ፦ ይህ ሰው ያለህን ይበትናል ብለው ከሰሱት።


ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር።


አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።


መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤


የዓመፃቸውን ደመወዝ ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ ነውረኞችና ርኵሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤


跟着我们:

广告


广告