Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 15:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንዲሁ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ ምክንያት በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ንስሓ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ ምክንያት በሰማይ በእግዚአብሔር መላእክት ዘንድ እንዲሁ ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ እን​ዲሁ ንስሓ ስለ​ሚ​ገባ ስለ አንድ ኀጢ​ኣ​ተኛ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት በሰ​ማ​ያት ደስታ ይሆ​ናል።”

参见章节 复制




ሉቃስ 15:10
23 交叉引用  

በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?


የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።


እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።


ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤


ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።


እንደዚሁ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም።


እላችሁማለሁ፥ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል፤


በሰውም ፊት የሚክደኝ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይካዳል።


ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።


እንዲህም አለ፦ አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት።


እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።


ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጐረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ፦ የጠፋውን ድሪሜን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች።


ስለዚህ እልሃለሁ፥ እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል።


ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና፦ “እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው” እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።


የጌታ መልአክ ግን በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ አወጣቸውና፦


እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።


ተቀብለህ ለዘላለም እንድትይዘው ስለዚህ ምናልባት ለጊዜው ተለይቶሃልና፤


ከቶ ለማን ብሎአል? ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?


跟着我们:

广告


广告