Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 11:48 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 እንግዲህ ለአባቶቻችሁ ሥራ ትመሰክራላችሁ ትስማማላችሁም፤ እነርሱ ገድለዋቸዋልና፥ እናንተም መቃብራቸውን ትሠራላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 እንግዲህ የአባቶቻችሁን ሥራ የምታጸኑ ምስክሮች ናችሁ፤ እነርሱ ነቢያትን ገደሉ፤ እናንተም መቃብራቸውን ታበጃጃላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 እንግዲህ በአባቶቻችሁ ሥራ ትስማማላችሁ፤ ስለ እርሱም ትመሰክራላችሁ፤ እነርሱ ገደሉአቸው እናንተ ደግሞ መቃብሮቻቸውን ትሠራላችሁና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 እንግዲህ አባቶቻችሁ ለገደሉአቸው ነቢያት መቃብሮቻቸውን በማሠራታችሁ እናንተ የክፉ ሥራቸው ተባባሪዎችና ምስክሮች ናችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሥራ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ የም​ት​መ​ሰ​ክ​ሩ​ባ​ቸ​ውም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ናችሁ፤ እነ​ርሱ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውን መቃ​ብ​ራ​ቸ​ውን እና​ንተ ትሠ​ራ​ላ​ች​ሁና።

参见章节 复制




ሉቃስ 11:48
14 交叉引用  

እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፥ ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል።


እናንተ ግን፦ ልጅ የአባቱን ኃጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን ባደረገ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና ባደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል።


እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።


እንግዲያስ የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሰክራላችሁ።


አባቶቻችሁ የገደሉአቸውን የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፥ ወዮላችሁ።


ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፦ ወደ እርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፥ ከእነርሱም ይገድላሉ ያሳድዱማል፥


እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም።


ወንድሞች ሆይ፥ የመከራና የትዕግሥት ምሳሌ የሆኑትን በጌታ ስም የተናገሩትን ነቢያትን ተመልከቱ።


ኢያሱም ሕዝቡን፦ እንድታመልኩት እናንተ እግዚአብሔርን እንደ መረጣችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ አላቸው፥ እነርሱም፦ ምስክሮች ነን አሉ።


跟着我们:

广告


广告