Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 1:36 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 እነሆ፤ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም በስተ እርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን የተባለችውም ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርሷ ደግሞ በስተርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን ትባል ለነበረችው ለእርሷም ይህ ስድስተኛ ወሯ ነው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ዘመድሽ ኤልሳቤጥ እንኳ መኻን ስትባል ኖራ አሁን በስተእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ ከፀነሰችም እነሆ፥ ስድስተኛ ወርዋ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እነሆ፥ ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ወገን የም​ት​ሆን ኤል​ሣ​ቤ​ጥም እር​ስዋ እንኳ በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ፀን​ሳ​ለች፤ መካን ትባል የነ​በ​ረ​ችው ከፀ​ነ​ሰች እነሆ፥ ይህ ስድ​ስ​ተኛ ወር ነው።

参见章节 复制




ሉቃስ 1:36
10 交叉引用  

ሦራም መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም።


የአብራም ሚስት ሦራ ግን ለአብራም ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ስምዋ አጋር የተባለ ግብፃዊት ባሪያም ነበረቻት


አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር።


ሣራም ፀነሰች እግዚአብሔርም በተናገረው ወራት ለአብርሃም በእርጅናው ወንድ ልጅን ወለደችለት።


ሴቲቱም ፀነሰች፤ በዚያም ወራት በአዲሱ ዓመት ኤልሳዕ እንዳላት ወንድ ልጅ ወለደች።


ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፥ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፥


መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።


ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።


በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።


ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቍኦጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች።


跟着我们:

广告


广告