Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 8:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያውን አደረገ፤ በመጠምጠሚያውም ላይ በፊቱ በኩል የተቀደሰውን አክሊል፥ ቅጠል የሚመስለውን የወርቅ ምልክት፥ አደረገ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት፣ ሙሴ መጠምጠሚያውን በአሮን ራስ ላይ አደረገ፤ በመጠምጠሚያው ላይ በፊት ለፊቱ በኩል የተቀደሰውን የወርቅ አክሊል አደረገለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያውን አደረገ፤ በመጠምጠሚያውም ላይ በፊቱ በኩል፥ የወርቅ ጉንጉን ሆኖ በቅጠል መልክ የተሠራውን የተቀደሰ አክሊል፥ አደረገ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በራሱም ላይ ጥምጥም አደረገለት፤ በጥምጥሙም ላይ ከፊት ለፊት በኩል እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በወርቅ አጊጦ የተሠራውን የቅድስና ምልክት የሆነውን አክሊል አኖረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በራሱ ላይ አክ​ሊል አደ​ረ​ገ​ለት፤ በአ​ክ​ሊ​ሉም ላይ በፊቱ በኩል የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን የወ​ርቅ መር​ገፍ አደ​ረገ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 8:9
10 交叉引用  

የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ የደረት ኪስ ኤፉድም ቀሚስም ዝንጕርጕር ሸሚዝም መጠምጠሚያም መታጠቂያም፤ እነዚህም ካህናት ይሆኑልኝ ዘንድ ለወንድምህ ለአሮን ለልጆቹም የተቀደሰ ልብስ ያድርጉ።


መጠምጠሚያውንም በራሱ ላይ ታደርጋለህ፥ የተቀደሰውንም አክሊል በመጠምጠሚያው ላይ ታኖራለህ።


ሙሴም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ።


የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አውራውን በግ ሁሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤ ይህ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ።


አሮንና ልጆቹም እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ።


ደግሞ፦ ንጹሕ ጥምጥም በራስ ላይ አድርጉ አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፥ የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር።


跟着我们:

广告


广告