Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 5:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከእነዚህ ነገሮች በአንዲቱ በደለኛ ሲሆን፥ የሠራውን ኃጢአት ይናዘዛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ማንኛውም ሰው ከእነዚህ በአንዱ በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣ የትኛውን ኀጢአት እንደ ሠራ ገልጾ መናዘዝ አለበት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አንድ ሰው ከእነዚህ ነገሮች በአንዱ በደለኛ ቢሆን፥ የሠራውን ኃጢአት ይናዘዛል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “አንድ ሰው ከእነዚህ ነገሮች በአንዲቱ በደለኛ ቢሆን የሠራውን ኃጢአት ይናዘዝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች በአ​ን​ዲቱ በደ​ለኛ ቢሆን፥ የሠ​ራ​ውን ኀጢ​አት ይና​ዘ​ዛል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 5:5
13 交叉引用  

እርሱም በሰው ፊት እየዘመረ፦ እኔ በድያለሁ፥ ቅኑንም አጣምሜአለሁ፥ የሚገባኝንም ብድራት አልተቀበልሁም፥


በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኃጢአትሽን ብቻ እወቂ ይላል እግዚአብሔር።


ወደ አምላኬም ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፥ ተናዝዤም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ ሆይ፥ ከሚወድዱህና ትእዛዝህን ከሚፈጽሙ ጋር ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና የምታስፈራ አምላክ ሆይ፥


አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ መተላለፋቸውንም ሁሉ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል።


በእኔም ላይ በእንቢተኝነት ስለ ሄዱብኝ የበደሉኝን በደል፥ ኃጢአታቸውንም፥ የአባቶቻቸውንም ኃጢአት ይናዘዛሉ።


ካህኑም ከእነዚያ በአንዳቸው ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። የተረፈውም እንደ እህል ቍርባን ለካህኑ ይሆናል።


የወሰደውንም በሙሉ ይመልስ አምስተኛውንም ይጨምርበት፥ ለበደለውም ሰው ይስጠው።


ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።


ኢያሱም አካንን፦ ልጄ ሆይ፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፥ ያደረግኸውንም ንገረኝ፥ አትሸሽገኝ አለው።


跟着我们:

广告


广告