Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 26:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፥ መቶውም አሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከእናንተ ዐምስቱ መቶውን፣ መቶውም ዐሥሩን ሺሕ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፥ መቶውም ዓሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በእናንተ ፊት በሰይፍ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከእናንተ አምስቱ መቶውን ጠላት ያሸንፋሉ፤ አንድ መቶው ደግሞ ዐሥሩን ሺህ ድል ይነሣሉ፤ ጠላቶቻችሁም በጦርነት ያልቃሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከእ​ና​ን​ተም አም​ስቱ መቶ​ውን ያሳ​ድ​ዳሉ፤ መቶ​ውም ዐሥ​ሩን ሺህ ያሳ​ድ​ዳሉ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በፊ​ታ​ችሁ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 26:8
15 交叉引用  

የዳዊትም ኀያላን ቍጥር ይህ ነበረ፤ የሠላሳው አለቃ የሐክሞናዊው ልጅ ያሾብዓም ነበረ፤ እርሱ ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰው በአንድ ጊዜ ገደለ።


የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ጦሩንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፤ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ።


የቀሩትም በንጉሡ አገር ያሉ አይሁድ ተሰብስበው ለሕይወታቸው ቆሙ፥ ከጠላቶቻቸውም ዐረፉ፥ ከሚጠሉአቸውም ሰባ አምስት ሺህ ገደሉ፥ ነገር ግን ወደ ብዝበዛው እጃቸውን አልዘረጉም።


ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ።


በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፥ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፥ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።


ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው።


ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ስደዱ ብሎ ተናገራቸው።


እግዚአብሔርም በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፥ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ።


እርሱ አምላካቸው ካልሸጣቸው፥ 2 እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ 2 አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር? 2 ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ ያሸሹ ነበር?


አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ተናገራችሁ ስለ እናንተ የሚዋጋ እርሱ ነውና ከእናንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳድዳል።


አዲስም የአህያ መንጋጋ አገኘ፥ እጁንም ዘርግቶ ወሰደው፥ በእርሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ።


跟着我们:

广告


广告