Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 24:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 መብራቱን ሁልጊዜ እንድታበራበት ለመብራት ጥሩ ተወቅጦ የተጠለለ የወይራ ዘይት ያመጡልህ ዘንድ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “መብራቶቹ ያለማቋረጥ እንዲያበሩ ለመብራቱ የሚሆን ከወይራ ተጨምቆ የተጠለለ ንጹሕ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን እዘዛቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “መብራቱ ሁልጊዜ እንዲበራ ለመብራቱ ተወቅጦ የተጠለለ ንጹሕ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “በድንኳኑ ውስጥ ያለው መብራት ዘወትር ሲበራ እንዲኖር ለማድረግ ተጨምቆ የተጠለለ ንጹሕ የወይራ ዘይት ያመጡልህ ዘንድ እስራኤላውያንን እዘዝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “መብ​ራ​ቱን ሁል ጊዜ እን​ድ​ታ​በ​ራ​በት ለመ​ብ​ራት ጥሩ ተወ​ቅጦ የተ​ጠ​ለለ የወ​ይራ ዘይት ያመ​ጡ​ልህ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እዘ​ዛ​ቸው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 24:2
27 交叉引用  

በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹን ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል።


ጥሩውንም መቅረዝ፥ መብራቶቹንም፥ በተራ የሚሆኑትንም ቀንዲሎች፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመብራቱንም ዘይት፤


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፥ በገበታው ፊት ለፊት፥ በማደሪያው በደቡብ በኩል አኖረ፤


የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።


ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ! እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም።


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


በምስክሩ መጋረጃ ውጭ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አሮን ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ ያሰናዳው፤ ለዘላለም ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ይሁን።


መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።


ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል።


ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤


በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።


ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።


እርሱ የሚያድንና የሚያበራ መብራት ነበረ፥ እናንተም ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ።


ደግሞም ኢየሱስ፦ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።


በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና።


跟着我们:

广告


广告