Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 17:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ስለዚህ የእስራኤል ልጆች በሜዳ የሚያርዱትን መሥዋዕታቸውን ወደ እግዚአብሔር ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያመጡታል፤ ወደ ካህኑም አምጥተው ለእግዚአብሔር ለደኅንነት መሥዋዕት ይሠዉታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እስራኤላውያን የሚሠዉትን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የሚያመጡበት ምክንያት ይህ ነው። ይህንም ካህኑ ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥተው ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት በማድረግ ያቅርቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በዚህም የእስራኤል ልጆች በሜዳ የሚያርዱትን መሥዋዕታቸውን እንዲያመጡ፥ ወደ ጌታ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ አምጥተዋቸው የአንድነት መሥዋዕት አድርገው ለጌታ እነርሱን እንዲያርዱ ለማድረግ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በሜዳ የሚያርዱትን መሥዋዕታቸውን ወደ እግዚአብሔር ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያመጡታል፤ ካህኑም ለእግዚአብሔር የአንድነት መሥዋዕት አድርጎ ያቀርበዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሜዳ የሚ​ያ​ር​ዱ​ትን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ያመ​ጡ​ታል፤ ወደ ካህ​ኑም አም​ጥ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕት ይሠ​ዉ​ታል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 17:5
20 交叉引用  

አብረሃምም በቤርሳቤህ የተምር ዛፍን ተከለ፤ በዚያም የዘላለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።


አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር አዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄደ በጉንም ወሰደው፦ በልጁም ፋንታ መሥውዕት አድርጎ ሠዋው።


የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሕቅን ይዘህ ወደ ሞሪያም ምድር ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መስዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ።


ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን ሠዋ ወንድሞቹንም እንጀራ እንዲበሉ ጠራ እነርሱም እንጀራን በሉ በዚያም በተራራ አደሩ።


እነርሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠሉ ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስገጃዎችንና ሐውልቶችን የማምለኪያ ዐፀዶችንም ለራሳቸው ሠሩ።


እስከዚያም ቀን ድረስ ለእግዚአብሔር ስም መቅደስ አልተሠራም ነበርና ሕዝቡ በኮረብታ ላይ ባሉት መስገጃዎች ይሠዋ ነበር።


ሰሎሞንም እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፤ በአባቱም በዳዊት ሥርዐት ይሄድ ነበር፤ ብቻ በኮረብታ መስገጃ ይሠዋና ያጥን ነበር።


በመስገጃዎችና በኮረብቶቹ ላይ በለመለመውም ዛፍ ሁሉ በታች ይሠዋና ያጥን ነበር።


በረጃጅሙ ኮረብታ ሁሉ ላይ በለመለመውም ዛፍ ሁሉ ታች ሐውልቶችንና የማምለኪያ ዐፀዶችን ተከሉ፤


በኮረብታው መስገጃዎችና በተራሮች ላይ በለመለመውም ዛፍ ሁሉ በታች ይሠዋና ያጥን ነበር።


የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ለእግዚአብሔርም ስለ ደኅንነት መሥዋዕት በሬዎችን እንዲሠዉ የእስራኤልን ልጆች ጎበዛዝት ሰደደ።


እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ ቅጠልማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፥ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቈጣኝን ቍርባናቸውን አቀረቡ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ።


ደምን ያፈስሱ ዘንድ ቀማኞች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ፥ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፥ በመካከልሽ ሴሰኝነትን አደረጉ።


ቀኖቹንም በፈጸሙ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ከዚያም በኋላ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን የደኅንነትንም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዓት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ፥ ስቡንና ደሙንም ወደ እኔ ያቀርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር ቍርባን ያቀርብ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአል፤ ያም ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።


ካህኑም በመገኛኛው ድንኳን ደጃፍ ባለው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ደሙን ይረጨዋል፥ ስቡንም ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ያቃጥለዋል።


እናንተ የምትወርሱአቸው አሕዛብ አማልክቶቻቸውን ያመለኩባቸውን በረጅም ተራሮች በኮረብቶችም ላይ ከለምለምም ዛፍ በታች ያለውን ስፍራ ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉአቸው፤


跟着我们:

广告


广告