Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 13:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ካህኑም በሥጋው ቁርበት ያለውን ደዌ ያያል፤ ጠጉሩም ተለውጦ ቢነጣ ደዌውም ወደ ሥጋው ቁርበት ቢጠልቅ፥ እርሱ የለምጽ ደዌ ነው፤ ካህኑም አይቶ፦ ርኩስ ነው ይበለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ካህኑም በሰውየው ቈዳ ላይ ያለውን ቍስል ይመርምር፤ በቍስሉ በተበከለው አካባቢ ያለው ጠጕር ወደ ነጭነት ተለውጦ ቢያገኘውና ቦታው ጐድጕዶ ወደ ውስጥ ቢገባ፣ ይህ ተላላፊ የቈዳ በሽታ ነው። ካህኑም መርምሮ ይህን ባወቀ ጊዜ፣ ሰውየው በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ርኩስ መሆኑ ይገለጽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ካህኑም በሰውነቱ ቆዳ ላይ ያለውን ደዌ ያያል፤ ጠጉሩም ተለውጦ ቢነጣ ደዌውም ከሰውነቱ ቆዳ በታች ዘልቆ ቢታይ፥ እርሱ የለምጽ ደዌ ነው፤ ካህኑም አይቶ፦ ርኩስ ነው ይበለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ካህኑም ቊስሉን ይመርምር፤ በዚያም ቊስል ላይ ያለው ጠጒር ወደ ነጭነት ቢለወጥ፥ ቊስሉም በዙሪያው ካለው ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ቢገኝ፥ እርሱ የሥጋ ደዌ በሽታ ነው፤ ካህኑም ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ካህ​ኑም በሥ​ጋው ቆዳ ያለ​ች​ውን ያችን ደዌ ይያት፤ ጠጕ​ሯም ተለ​ውጣ ብት​ነጣ በሥ​ጋው ቆዳ ያለች የዚ​ያች ደዌ መልክ ቢከፋ፥ ደዌ​ውም ወደ ሥጋው ቆዳ ቢጠ​ልቅ፥ እር​ስዋ የለ​ምጽ ደዌ ናት፤ ካህ​ኑም አይቶ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይበ​ለው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 13:3
29 交叉引用  

ከአዜብ ባደረገው በጉዞውም ወደ ቤቴል በኩል ሄደ ያም ስፍራ አስቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳን ተክሎበት የነበረው ነው፤


የማታፍረውን የጋለሞታን ሥራ ሁሉ ሠርተሻልና ልብሽ ምንኛ ደካማ ነው? ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ይለዩ ዘንድ ሕዝቤን ያስተምሩ፥ ንጹሕና ንጹሕ ባልሆነው መካከል ይለዩ ዘንድ ያሳዩአቸው።


እንግዶች ጕልበቱን በሉት፥ እርሱም አላወቀም፥ ሽበትም ወጣበት፥ እርሱም አላወቀም።


በተቀደሰውና ባልተቀደሰው፥ በርኩሱና በንጹሑም መካከል ትለያላችሁ፤


ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ በቁርበቱ ላይ ነጭ እባጭ ቢሆን፥ ጠጉሩም ተለውጦ ቢነጣ፥ ሥጋውም በእባጩ ውስጥ ቢያዥ፥


ማናቸውም ሰው በሥጋው ቁርበት ላይ እባጭ ወይም ብጉር ወይም ቍቁቻ ቢታይ፥ በሥጋው ቁርበት እንደ ለምጽ ደዌ ቢመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካህናቱ ልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት።


ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ ወደ ቁርበቱ ውስጥ ጠልቆ ቢታይ፥ ጠጉሩም ተለውጦ ቢነጣ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው፤ ከቍስሉ ውስጥ ወጥቶአል።


ቍቁቻውም በሥጋው ቁርበት ላይ ቢነጣ፥ ከቁርበቱም የጠለቀ ባይመስል፥ ጠጉሩም ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይዘጋበታል።


ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ እከኩ በቁርበቱ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ለምጽ ነው።


ደዌውንም ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በግንቡ ላይ በአረንጓዴና በቀይ ቢዥጐረጐር፥ መልኩም ወደ ግንቡ ውስጥ ቢጠልቅ፥


ይህም ሕግ ነው ለሁሉ ዓይነት ለምጽ ደዌ፥


ለእባጭም፥ ለብጕርም፥ ለቍቁቻም፤


ወይም ርኩስነቱን ሳያውቅ ርኩስን ሰው ቢነካ፥ በማናቸውም ርኩሰት ቢረክስ፥ ነገሩ በታወቀው ጊዜ በደል ይሆንበታል።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ካህናቱን ስለ ሕጉ ጠይቅ፥


ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።


የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።


ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” አላቸው።


በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ፦ አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና።


ከእነዚያም፥ እንዳይሳደቡ ይማሩ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው፥ ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ናቸው።


ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።


የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


跟着我们:

广告


广告