Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 12:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት፤ እንደ ሕመምዋ መርገም ወራት ትረክሳለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ሴት አርግዛ ወንድ ልጅ በምትወልድበት ጊዜ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ እስከ ሰባት ቀን ትረክሳለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ሴት ፀንሳ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያኽል የረከሰች ትሆናለች፤ እንደ ወር አበባዋም ጊዜያት ትረክሳለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ሴት ፀንሳ ወንድ ልጅ ብትወልድ፥ በወር አበባዋ እንደሚሆነው ዐይነት እስከ ሰባት ቀን ድረስ የረከሰች ትሆናለች፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ ሴት ብታ​ረ​ግዝ ወንድ ልጅም ብት​ወ​ልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 12:2
14 交叉引用  

እግዚአብሔርም ባረካቸዉ፤ እንዲህም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትም ሁሉ ግዙአቸዉ።


ለሴቲቱም አለ፤ በፀነሰሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።


ዳዊትም መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፥ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኩሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፥ ወደ ቤትዋም ተመለሰች።


ከርኩስ ነገር ንጹሕን ሊያወጣ ማን ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም።


ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድር ነው?


ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፥ ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል?


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ሴት ልጅም ብትወልድ እንደ መርገምዋ ወራት ሁለት ሳምንት ያህል የረከሰች ናት፤ ከደምዋም እስክትነጻ ድረስ ስድሳ ስድስት ቀን ትቀመጥ።


ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት በሥጋዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን፥ በመርገምዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤ የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።


እርስዋም በመርገምዋ ርኵሰት ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ወደ ሴት አትቅረብ።


ወይም ርኩስነቱን ሳያውቅ ርኩስን ሰው ቢነካ፥ በማናቸውም ርኩሰት ቢረክስ፥ ነገሩ በታወቀው ጊዜ በደል ይሆንበታል።


እንደ ሙሴም ሕግ የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥ በጌታ ሕግ፦ የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ተብሎ እንደ ተጻፈ በጌታ ፊት ሊያቆሙት፥ በጌታም ሕግ፦ ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት።


跟着我们:

广告


广告