Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 10:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የእግዚአብሔር የቅብዓት ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትወጡም አላቸው። እንደ ሙሴ ቃልም አደረጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የእግዚአብሔር የመቅቢያ ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን አትውጡ።” እነርሱም ሙሴ እንዳላቸው አደረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንዲሁም የጌታ የቅባት ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትውጡ።” እንደ ሙሴ ቃልም አደረጉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ባዘዘው የቅባት ዘይት የተቀደሳችሁ ስለ ሆነ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ውጪ አትውጡ፤ አለበለዚያ ትሞታላችሁ፤” አላቸው፤ እነርሱም ሙሴ እንዳዘዛቸው አደረጉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቅ​ብ​ዐት ዘይት በላ​ያ​ችሁ ነውና እን​ዳ​ት​ሞቱ ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አት​ውጡ” አላ​ቸው። ሙሴም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 10:7
12 交叉引用  

ይህንም ሁሉ ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ታለብሳቸዋለህ፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፥ ትክናቸዋለህ፥ ትቀድሳቸውማለህ።


የቅብዓትንም ዘይት ወስደህ በራሱ ላይ ታፈስሰዋለህ፥ ትቀባውማለህ።


በክህነትም ያገለግሉኝ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን ቅባቸው፥ ቀድሳቸውም።


እግዚአብሔርም አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


የአምላኩም ቅባት ዘይት ቅዱስነት በላዩ ነውና ከመቅደስ አይውጣ፥ የአምላኩንም መቅደስ አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ከቅብዓቱም ዘይት በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰ፥ ይቀድሰውም ዘንድ ቀባው።


ሙሴም ከቅብዓቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም፥ የልጆቹንም ልብስ ቀደሰ።


ኢየሱስም፦ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ አለው።


እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤


በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፥


跟着我们:

广告


广告