Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን፦ እንዳትሞቱ በማኅበሩም ሁሉ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ራሳችሁን አትንጩ፥ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ እግዚአብሔር ስላቃጠለው ማቃጠል ግን ወንድሞቻችሁ የእስራኤል ቤት ሁሉ ያልቅሱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሙሴም አሮንንና የአሮንን ልጆች፣ አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፤ “እንዳትሞቱ፣ በሕዝቡም ላይ ቍጣ እንዳይመጣ ጠጕራችሁን አትንጩ፤ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በእሳት ስላጠፋቸው ሰዎች ወንድሞቻችሁ እስራኤላውያን ሊያለቅሱላቸው ይችላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እንዳትሞቱ በማኅበሩም ሁሉ ላይ እርሱ እንዳይቈጣ የራሳችሁን ጠጉር አታጐስቁሉ፥ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ጌታ እሳትን ልኮ ስላደረገው ማቃጠል ግን ወንድሞቻችሁ የእስራኤል ቤት ሁሉ ያልቅሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚህ በኋላ ሙሴ አሮንን፥ እንዲሁም አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ሁለቱን የአሮንን ልጆች እንዲህ አላቸው፤ “ለሐዘን ብላችሁ ጠጒራችሁን አትላጩ፤ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ይህን ብታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ቊጣውን ያወርዳል፤ ነገር ግን ወንድሞቻችሁ እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር በተላከ እሳት ስለሞቱት ልጆች እንዲያለቅሱ ተፈቅዶላቸዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሙሴም አሮ​ንን፥ ልጆ​ቹ​ንም አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን፥ “እን​ዳ​ት​ሞቱ፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ላይ ሁሉ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ራሳ​ች​ሁን አት​ንጩ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም አት​ቅ​ደዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስላ​ቃ​ጠ​ላ​ቸው ማቃ​ጠል ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ያል​ቅሱ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 10:6
23 交叉引用  

ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ዳዊትም፦ ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር ብሎ በላያቸው አስነሣው።


የአቢሱ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የአልዓዛር ልጅ፥ የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ፤


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ለእስራኤል ልጆች፦ እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፥ አንድ ጊዜ በእናንተ መካከል ብወጣ አጠፋችኋለሁ፤ አሁንም የማደርግባችሁን አውቅ ዘንድ ጌጣችሁን ከእናንተ አውጡ በላቸው አለው።


አሮንም የአሚናዳብን የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርስዋም ዮናዳብንና አብድን አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።


እግዚአብሔር የቍጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጕርሽን ቍረጪ፥ ጣዪውም፥ በወናዎች ኮረብቶችም ላይ አሙሺ።


የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥ ራሱም የተገለጠ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ርኩስ ነኝ ይበል።


ተማርከው ከአንቺ ዘንድ ወጥተዋልና ስለ ተድላሽ ልጆች ራስሽን ንጪ፥ ጠጕርሽንም ተቈረጪ፥ ቡሃነትሽንም እንደ ንስር አስፊ።


ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ቍጣ እንዳይወርድ ሌዋውያን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያንም የምስክሩን ማደሪያ ይጠብቁ።


ምድርን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤


እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው፦ አምላክ ሆይ፥ አንተ የሰው ሁሉ ነፍስ አምላክ፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን? አሉ።


እንደ ገና በእስራኤል ልጆች ላይ ቍጣ እንዳይሆንባቸው እናንተ መቅደሱንና መሠዊያውን ጠብቁ።


አሮንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ ላይ አምጣቸው፤


ካህኑም ሴቲቱን በእግዚአብሔር ፊት ያቆማታል፥ የሴቲቱንም ራስ ይገልጣል፥ በእጅዋም ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል ቍርባን፥ ለቅንዓት ቍርባን፥ ያኖራል፤ በካህኑም እጅ እርግማንን የሚያመጣው መራራ ውኃ ይሆናል።


ስለ አባቱና ስለ እናቱ፦ አላየሁም ላለ፥ 2 ወንድሞቹንም ላላስተዋለ፥ 2 ልጆቹንም ላላወቀ፤ 2 ቃልህን አደረጉ፥ 2 ቃል ኪዳንህንም ጠበቁ።


እናንተ ዛሬ እግዚአብሔርን ከመከተል ትመለሳላችሁን? ዛሬ በእግዚአብሔር ላይ ብታምፁ ነገ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ይቈጣል።


የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ኃጢአትን ስለ ሠራ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቁጣ አልወረደምን? እርሱም በኃጢአቱ ብቻውን አልሞተም።


የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር በደሉ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፥ የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።


እስራኤል በድሎአል፥ ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል፥ እርም የሆነውንም ነገር ወሰዱ፥ ሰረቁም፥ ዋሹም፥ በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።


跟着我们:

广告


广告