Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 5:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፥ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የሚያሳድዱን ከተረከዞቻችን ሥር ናቸው፤ ተጨንቀናል ዕረፍትም ዐጥተናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፥ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ቀንበር እንደተጫኑ እንስሶች በመነዳት እጅግ ደክመናል፤ እንድናርፍም አይፈቀድልንም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሳ​ደ​ዱን፤ እኛም ደክ​መ​ናል፤ ዕረ​ፍ​ትም የለ​ንም።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 5:5
14 交叉引用  

እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ እስራትና ቀንበር ሥራ በአንገትህም ላይ አድርግ፥


ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማይገዛውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ይገዙለት ዘንድ የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ፥ እነርሱም ይገዙለታል፥ የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰፊው የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል ረጃጅሞችም በሮችዋ በእሳት ይቃጠላሉ፥ የወገኖችም ድካም ከንቱ ትሆናለች፥ የአሕዛብም ሥራ ለእሳት ትሆናለች፥ እነርሱም ይደክማሉ።


ኖን። የኃጢአቶቼ ቀንበር በእጁ ተይዛለች፥ ታስረው በአንገቴ ላይ ወጥተዋል፥ ጕልበቴን አደከመ። ጌታ በፊታቸው እቆም ዘንድ በማልችላቸው እጅ አሳልፎ ሰጠኝ።


ጋሜል። ይሁዳ ስለ መጨነቅና ስለ ባርነት ብዛት ተማረከች፥ በአሕዛብ መካከል ተቀመጠች ዕረፍትም አላገኘችም፥ የሚያስጨንቁአት ሁሉ ተጨንቃ አገኙአት።


ቆፍ። አሳዳጆቻችን ከሰማይ ንስር ይልቅ ፈጣኖች ሆኑ፥ በተራሮች ላይ አሳደዱን፥ በምድረ በዳ ሸመቁብን።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።


ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤


እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለ ምን ትፈታተናላችሁ?


በራብና በጥማት በዕራቁትነትም ሁሉንም በማጣት እግዚአብሔር ለሚልክብህ ለጠላቶችህ ትገዛለህ፤ እስኪያጠፋህም ድረስ በአንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭናል።


跟着我们:

广告


广告