Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 4:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ዔ። የእግዚአብሔር ፊት በተናቸው እርሱም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፥ የካህናቱን ፊት አላፈሩም፥ ሽማግሌዎቹንም አላከበሩም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔር ራሱ በትኗቸዋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ አይጠብቃቸውም፤ ካህናቱ አልተከበሩም፤ ሽማግሌዎቹም ከበሬታ አላገኙም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ዔ። የእግዚአብሔር ፊት በተናቸው እርሱም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፥ የካህናቱን ፊት አላፈሩም፥ ሽማግሌዎቹንም አላከበሩም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔር ራሱ የበተናቸው ስለ ሆነ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ እነርሱ አያስብም፤ ለካህናቱ ክብር አይሰጣቸውም፤ ሽማግሌዎችም ልዩ አስተያየት አይደረግላቸውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ዔ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፍ​ላ​ቸው ነበረ። ነገር ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸ​ውም፤ የካ​ህ​ና​ቱን ፊት አላ​ፈ​ሩም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም አላ​ከ​በ​ሩም።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 4:16
20 交叉引用  

ቍጣቸው ርጉም ይሁን ጽኑ ነበርና ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።


ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተመቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።


እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ፥ እንደ ባሪያውም እንዲሁ ጌታው፥ እንደ ባሪያይቱም እንዲሁ እመቤትዋ፥ እንደሚገዛም እንዲሁ የሚሸጠው፥ እንደ አበዳሪውም እንዲሁ ተበዳሪው፥ እንደ ዕዳ አስከፋዩም እንዲሁ ዕዳ ከፋዩ ይሆናል።


በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር ርስቴንም አረከስሁ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፥ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።


የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ በምድር መንግሥታት ሁሉ መካከል ለመከራ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን ሦስቱንም በረኞች ወሰደ፥


ሬስ። አቤቱ፥ እይ፥ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት፥ ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በጌታ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?


ዋው። ማደሪያውን እንደ አትክልት ነቀለ፥ የበዓሉን ስፍራ አጠፋ፥ እግዚአብሔር በጽዮን ዓመት በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፥ በቍጣውም መዓት ንጉሡንና ካህኑን አቃለለ።


አለቆች በእጃቸው ተሰቀሉ፥ የሽማግሌዎች ፊት አልታፈረም።


ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፥ ፍርድንም አደርግብሻለሁ ከአንቺም የቀረውን ሁሉ ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ።


እግዚአብሔር ከጠላቶችህ ፊት የተመታህ ያደርግሃል፤ በአንድ መንገድ ትወጣባቸዋለህ፥ በሰባት መንገድ ከእነርሱ ትሸሻለህ፤ ለምድርም መንግሥታት ሁሉ ድንጋጤ ትሆናለህ።


እበትናቸዋለሁ አልሁ፤ 2 ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ።


ከግብፅ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው ይላል ጌታ።


跟着我们:

广告


广告