Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 2:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ቤት። ጌታ የያዕቆብን ማደሪያዎች ሁሉ ዋጠ፥ አልራራምም፥ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አምቦች አፈረሰ፥ ወደ ምድርም አወረዳቸው መንግሥቱንና አለቆችዋን አረከሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የያዕቆብን መኖሪያ ሁሉ፣ ጌታ ያለ ርኅራኄ ዋጣቸው፤ የይሁዳን ሴት ልጅ ምሽጎች፣ በቍጣው አፈረሳቸው፤ መንግሥቷንና መሳፍንቷን፣ በማዋረድ ወደ ምድር ጣላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ቤት። ጌታ የያዕቆብን ማደሪያዎች ሁሉ ዋጠ፥ አልራራምም፥ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አምቦች አፈረሰ፥ ወደ ምድርም አወረዳቸው መንግሥቱንና አለቆችዋን አረከሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ጌታ የእስራኤልን መኖሪያ ሁሉ ያለ ምሕረት አጠፋ፤ በቊጣውም የይሁዳን ሕዝብ ምሽግ አፈረሰ፤ መንግሥትዋንና ባለ ሥልጣኖቿን ወደ ምድር ጥሎ አዋረደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ቤት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የያ​ዕ​ቆ​ብን መል​ካም ነገር ሁሉ አሰ​ጠመ፤ አል​ራ​ራ​ምም፤ በመ​ዓቱ የይ​ሁ​ዳን ሴት ልጅ አን​ባ​ዎች አፈ​ረሰ፤ ወደ ምድ​ርም አወ​ረ​ዳ​ቸው፤ መን​ግ​ሥ​ቷ​ንና ግዛ​ቷ​ንም አረ​ከሰ።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 2:2
32 交叉引用  

እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ በውኑ ባሪያዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም፥ በከንቱም አጠፋው ዘንድ አንተ በእርሱ ላይ ምንም ብታንቀሳቅሰኝ፥ እስከ አሁን ፍጹምነቱን ይዞአል።


ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የድንጋጤና የመረገጥ የድብልቅልቅም ቀን፥ የቅጥርን መፍረስ ወደ ተራራ መጮኽ በራእይ ሸለቆ ውስጥ ሆኖአል።


የክብርን ሁሉ ትዕቢት ይሽር ዘንድ የምድርንም ክቡራን ሁሉ ያስንቅ ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖታል።


የተመሸገውንም ከፍ ከፍ ያለውንም ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፥ ያዋርደውማል፥ ወደ መሬትም እስከ አፈር ድረስ ይጥለዋል።


በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፥ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፥ እስከ መሬትም ድረስ ያወርዳታል፥ እስከ አፈርም ድረስ ይጥላታል።


ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፥ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።


ስለዚህ የመቅደሱን አለቆች አረከስሁ፥ ያዕቆብንም እርግማን፥ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ።


በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር ርስቴንም አረከስሁ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፥ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።


ሰውንም በሰው ላይ፥ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ፥ እቀጠቅጣቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራም፥ አላዝንም፥ አልምርም።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ፥ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።


ከዚህ በኋላ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትንም ባሪዎቹንና ሕዝቡን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፥ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፥ አያዝንላቸውም፥ አይራራላቸውም፥ አይምራቸውም።


ወደ ቅጥርዋ ወጥታችሁ አፍርሱ፥ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፥ ለእግዚአብሔር አይደሉምና ቅርንጫፍዋን ውሰዱ።


ፌ። እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፥ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውን ቃል ፈጸመ፥ አፈረሰ አልራራምም፥ ጠላትንም ደስ አሰኘብሽ፥ የሚያስጨንቁሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ።


ሳን። ብላቴናውና ሽማግሌው በመንገዶች ላይ ተጋደሙ፥ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ በሰይፍ ወድቀዋል፥ በቍጣህ ቀን ገደልሃቸው፥ ሳትራራ አረድሃቸው።


ሄ። ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፥ እስራኤልን ዋጠ፥ አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፥ አምቦችዋን አጠፋ፥ በይሁዳም ሴት ልጅ ኀዘንና ልቅሶ አበዛ።


ሳምኬት። በቍጣ ከደንኸን አሳደድኸንም፥ ገደልኸን፥ አልራራህም።


ስለዚህ፥ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም።


ዓይኔም አይራራልሽም እኔም አላዝንም፥ መንገድሽንም አመጣብሻለሁ ርኵሰትሽም በመካከልሽ ይሆናል፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም፥ እንደ መንገድሽም መጠን አመጣብሻለሁ፥ ርኵሰትሽም በመካከልሽ ይሆናል፥ እኔም እግዚአብሔር የምቀሥፍ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


ስለዚህ እኔ ደግሞ በመዓት እሠራለሁ፥ ዓይኔ አይራራም እኔም አላዝንም፥ ወደ ጆሮዬም በታላቅ ድምፅ ቢጮኹ አልሰማቸውም አለኝ።


እኔም ደግሞ በዓይኔ አልራራም አላዝንምም፥ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ አለኝ።


የማምለኪያ ዐፀዶችህንም ከመካከልህ እነቅላለሁ፥ ከተሞችህንም አፈርሳለሁ።


ኤዶምያስ፦ እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፥ በሰዎችም ዘንድ፦ የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።


እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው።


የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤


በአገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ደጆች ሁሉ ከብበው ያስጭንቁሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ በደጆች ሁሉ ከብበው ያስጨንቁሃል።


እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለችና፥ 2 እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፥ 2 ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፥ 2 የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።


跟着我们:

广告


广告