Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 9:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልመቱአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጉረመረሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሆኖም እስራኤላውያን አልወጓቸውም፤ የጉባኤው መሪዎች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ምለውላቸው ነበርና። ማኅበሩም ሁሉ በመሪዎቹ ላይ አጕረመረሙ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በጌታ ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልመቱአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጉረመረሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የሕዝቡ መሪዎች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ምለውላቸው ስለ ነበረ እስራኤላውያን እነርሱን አልገደሉአቸውም። ስለዚሁም ጉዳይ እስራኤላውያን ሁሉ በመሪዎቻቸው ላይ አጒረመረሙ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ማሉ​ላ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አል​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውም። ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በአ​ለ​ቆቹ ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ።

参见章节 复制




ኢያሱ 9:18
11 交叉引用  

ንጉሡም በሳኦል ልጅ በዮናታንና በዳዊት መካከል ስለ ነበረው ስለ እግዚአብሔር መሐላ የሳኦልን ልጅ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን አዳነ።


እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል፥ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።


ሥጋህን በኃጢአት እንዳያስተው ለአፍህ አርነት አትስጥ፥ በመልአክም ፊት፦ ስሕተት ነበረ አትበል፥ እግዚአብሔር በቃልህ ይቈጣ ዘንድ የእጅህንም ሥራ ያጠፋ ዘንድ ስለምን ትሻለህ?


የጻድቁና የበደለኛው፥ የመልካሙና የክፉው፥ የንጹሑና የርኩሱ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋውና የማይሠዋው፥ የሰው ሁሉ ድርሻው አንድ ነው፥ እንደ መልካሙ ሰው እንዲሁ ኃጢአተኛው፥ እንደ መሐለኛው ሰው እንዲሁ መሐላን የሚፈራው ነው።


ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ራስዋን በመሐላ ብታስር፥


ባትሳል ግን ኃጢአት የለብህም።


በአፍህ የተናገርኸውን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በፈቃድህ ተስለሃልና ከከንፈርህ የወጣውን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።


ወደ ባልንጀራህ ወይን ቦታ በገባህ ጊዜ እስክትጠግብ ድረስ ከወይኑ ብላ፤ ወደ ዕቃህ ግን ከእርሱ ምንም አታግባ።


የእስራኤልም ልጆች ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ፥ የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያትይዓሪም ነበረ።


አለቆቹም ሁሉ ለማኅበሩ ሁሉ፦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ምለንላቸዋል፥ ስለዚህም እንነካቸው ዘንድ አይገባንም።


跟着我们:

广告


广告