Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 9:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የእስራኤልም ልጆች ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ፥ የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያትይዓሪም ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ እስራኤላውያን ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ገባዖን፣ ከፊራ፣ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ወደተባሉት የገባዖን ሰዎች ወደሚኖሩባቸው ከተሞች መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የእስራኤልም ልጆች ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ፤ ከተሞቻቸው ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያት-ይዓሪም ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጒዞ ጀምረው ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሕዝብ ወደሚኖሩባቸው ከተሞች ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ በኤሮትና ቂርያትይዓሪም ተብለው ይጠሩ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጕ​ዘው በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ደረሱ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ገባ​ዖን፥ ከፊራ፥ ብኤ​ሮ​ትና ኢያ​ሪም ነበሩ።

参见章节 复制




ኢያሱ 9:17
24 交叉引用  

ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፥ የአንዱም ስም በዓና፥ የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፥ ከብንያምም ልጆች የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ነበሩ፥ ብኤሮትም ለብንያም ተቆጥራ ነበር።


ገባዖናዊው ሰማያስ፥ እርሱ በሠላሳው መካከልና በሠላሳው ላይ ኀያል ሰው ነበረ፤ ኤርምያስ፥ የሕዚኤል፥ ዮሐናን፥ ገድሮታዊ ዮዛባት፥


የካሌብ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጅ የቂርያትይዓሪም አባት ሦባል፥


ለቂርያትይዓሪምም አባት ለሦባል ልጆች ነበሩት፤ ሀሮኤ የመናሕታውያን እኵሌታ።


የቂርያትይዓሪምም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፉታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሽራውያን፤ ከእነዚህም ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ወጡ።


ሙሴም በምድረ በዳ የሠራት የእግዚአብሔር ማደሪያና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው መሠዊያ በዚያን ጊዜ በገባዖን ባለው በኮረብታው መስገጃ ነበሩ።


የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ልጆች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት።


የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ሰዎች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት።


ደግሞም በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፥ እርሱም የቂርያትይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፥ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ እንደ ኤርምያስ ቃል ሁሉ ትንቢት ተናገረ።


ገባዖን ከመንግሥታት ከተሞች እንደ አንዲቱ ታላቅ ከተማ ስለ ሆነች፥ ከጋይም ስለ በለጠች፥ ሰዎችዋም ሁሉ ኃያላን ስለ ነበሩ፥ እጅግ ፈራ።


ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያትበኣል፥ ረባት፥ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።


ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ፥ ቂርያትይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ደረሰ።


ድንበሩም ወደ ምዕራብ ሄደ፥ በቤትሖሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ዞረ፥ መውጫውም ቂርያትይዓሪም በምትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያትበኣል ነበረ፥ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።


የደቡብም ዳርቻ ከቂርያትይዓሪም መጨረሻ ነበረ፥ ድንበሩም በምዕራቡ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ወጣ።


ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ ጎረቤቶቻቸው እንደ ሆኑ በመካከላቸውም እንደ ኖሩ ሰሙ።


የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልመቱአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጉረመረሙ።


የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥


እነርሱም አሉት፦ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር ባሪያዎችህ መጥተናል፥ ዝናውንም፥ በግብፅም ያደረገውን ሁሉ፥


ወጥተውም በይሁዳ ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፥ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፥ እነሆም፥ ከቂርያትይዓሪም በስተ ኋላ ነው።


በቂርያትይዓሪምም ወደ ተቀመጡት ሰዎች መልክተኞች ልከው፦ ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰዋል፥ ወርዳችሁም ወደ እናንተ አውጡት አሉ።


የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት አወጡ፥ በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡት፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።


跟着我们:

广告


广告