Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 9:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሰዎቹም ከስንቃቸው ወሰዱ፥ እግዚአብሔርንም አልጠየቁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የእስራኤልም ሰዎች ከስንቃቸው ላይ ጥቂት ወሰዱ፤ ስለ ጕዳዩ ግን እግዚአብሔርን አልጠየቁም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የእስራኤልም አለቆች ከስንቃቸው ወሰዱ፥ የጌታንም ምሪት አልጠየቁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የእስራኤልም ሰዎች ከመንገደኞቹ ስንቅ ጥቂት ወሰዱ፤ ስለ ሁኔታው ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ አልጠየቁም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አለ​ቆ​ችም ከስ​ን​ቃ​ቸው ወሰዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ጠ​የ​ቁም።

参见章节 复制




ኢያሱ 9:14
17 交叉引用  

ከዚያም በኋላ ዳዊት፦ ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፦ ውጣ አለው። ዳዊትም፦ ወዴት ልውጣ? አለ። እርሱም፦ ወደ ኬብሮን ውጣ አለው።


ዳዊትም፦ ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ፍልስጥኤማውያንን በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ አለው።


በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።


በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።


በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።


ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።


እነዚህም የጠጅ አቁማዳዎች አዲስ ሳሉ ሞላንባቸው፥ እነሆም፥ ተቀድደዋል፥ መንገዳችንም እጅግ ስለ ራቀብን እነዚህ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።


እንዲህም ሆነ፥ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች፦ ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን በፊት ይወጣልናል? ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ።


የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፥ እግዚአብሔርንም፦ የብንያምን ልጆች ለመውጋት አስቀድሞ ማን ይውጣልን? ብለው ጠየቁት፥ እግዚአብሔርም፦ ይሁዳ ይቅደም አለ።


እግዚአብሔርንም ጠየቀለት፥ ስንቅንም ሰጠው፥ የፍልስጥኤማዊውንም የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው አለው።


跟着我们:

广告


广告