Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 6:26 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በዚያን ጊዜም ኢያሱ፦ ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ርጉም ይሁን፥ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ ብሎ ማለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚያ ጊዜም ኢያሱ፣ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ይህች ከተማ ኢያሪኮን መልሶ የሚሠራት ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን፤ “መሠረቷን ሲጥል፣ የበኵር ልጁ ይጥፋ፤ ቅጥሮቿንም ሲያቆም፣ የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ” ብሎ ማለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በጌታ ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በዚያን ጊዜ ኢያሱ፦ “ይህቺን የኢያሪኮን ከተማ ለመገንባት የሚነሣ የተረገመ ይሁን፤ መሠረቱን ሲጥል የበኲር ልጁ ይጥፋ፤ መዝጊያውን ሲያቆም የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ፤” ብሎ ረገመ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በዚ​ያ​ችም ቀን ኢያሱ፥ “ይህ​ችን ከተማ ኢያ​ሪ​ኮን ለመ​ሥ​ራት የሚ​ነሣ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠ​ረ​ቷን በበ​ኵር ልጁ የሚ​ጥል፥ በሮ​ች​ዋ​ንም በታ​ናሹ ልጁ የሚ​ያ​ቆም ርጉም ይሁን” ብሎ ማለ።

参见章节 复制




ኢያሱ 6:26
9 交叉引用  

በእርሱም ዘመን የቤቴል ሰው አኪኤል ኢያሪኮን ሠራ፤ በነዌም ልጅ በኢያሱ አማካይነት እንደ ተነገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ በበኵር ልጁ በአቢሮን መሠረትዋን አደረገ፤ በታናሹ ልጁም በሠጉብ በሮችዋን አቆመ።


ንጉሡም “ከእውነት በቀር በእግዚአብሔር ስም እንዳትነግረኝ ስንት ጊዜ አምልሃለሁ?” አለው።


ኤልያስም “ኤልሳዕ ሆይ! እግዚአብሔር ወደ ኢያሪኮ ልኮኛልና እባክህ፥ በዚህ ቆይ፤” አለው። እርሱም “ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ አልለይህም” አለ። ወደ ኢያሪኮም መጡ።


ኤዶምያስ፦ እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፥ በሰዎችም ዘንድ፦ የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም፦ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ አለው።


አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች፦ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።


ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፥ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ ወደ ዮርዳኖስም ወጣ።


跟着我们:

广告


广告