ኢያሱ 6:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ኢያሱም ሕዝቡን፦ እኔ፦ ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ አትጩኹ፥ ድምፃችሁንም አታንሡ፥ ከአፋችሁም አንድ ቃል አይውጣ፥ በዚያን ጊዜ ትጮኻላችሁ ብሎ አዘዛቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ኢያሱ ሕዝቡን፣ “የማሸበሪያ ጩኸት አታሰሙ፤ ድምፃችሁ ከፍ ብሎ አይሰማ፤ ጩኹ እስከምላችሁም ቀን ድረስ ከአፋችሁ አንዲት ቃል አትውጣ፤ የምትጮኹት ከዚያ በኋላ ነው” ሲል አዘዛቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “እኔ፦ ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ አትጩኹ፥ ድምፃችሁንም አታሰሙ፥ ከአፋችሁም አንድ ቃል አይውጣ፤ ከዚያን በኋላ ግን ትጮኻላችሁ።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ኢያሱ ግን፦ “ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ እንዳትጮኹ፤ ወይም ድምፃችሁ እንዳይሰማ፤ እንዲያውም አንዲት ቃል እንኳ እንዳትናገሩ፤ ጩኹ ስላችሁ በዚያን ጊዜ ትጮኻላችሁ” ብሎ ሕዝቡን አዘዘ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ኢያሱም ሕዝቡን፦ እንዳይጮኹ ማንም ድምፃቸውን እንዳይሰማ፥ እንዲጮኹ እስኪያዛቸውም ድረስ ከአፋቸው ቃል እንዳይወጣ አዘዛቸው። 参见章节 |