Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 5:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፥ ነገር ግን ከግብፅ በወጡበት መንገድ በምድረ በዳ የተወለዱት ሕዝብ ሁሉ አልተገረዙም ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዚያ የወጡት ሰዎች ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ከግብጽ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ በጕዞ ላይ ሳሉ የተወለዱት ግን በሙሉ አልተገረዙም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ነገር ግን ከግብጽ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ በመንገድ እየተጓዙ ሳሉ የተወለዱት ልጆች ሁሉ አልተገረዙም ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በመጀመሪያ ከግብጽ ምድር የወጡት ወንዶች ሁሉ ተገርዘው የነበሩ ቢሆኑም እንኳ በበረሓው ጒዞ ጊዜ የተወለዱት ወንዶች አልተገረዙም ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ነገር ግን ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ፥ በም​ድረ በዳ የተ​ወ​ለዱ ሕዝብ ሁሉ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና፥ ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ገረ​ዛ​ቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 5:5
9 交叉引用  

ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ብታውቁስ ኃጢአት የሌለባቸውን ባልኵኦነናችሁም ነበር።


እንግዲህ ያልተገረዘ ሰው የሕግን ሥርዓት ቢጠብቅ አለመገረዙ እንደ መገረዝ ሆኖ አይቈጠርለትምን?


መገረዝ ቢሆን አለመገረዝም ቢሆን ከንቱ ነው፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ።


በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።


በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።


ኢያሱ የገረዘበትም ምክንያት ይህ ነው፥ ከግብፅ የወጡት ሕዝብ ወንዶች ሰልፈኞች ሁሉ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞቱ።


እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዳያሳያቸው የማለላቸው፥ ከግብፅ የወጡ የእግዚአብሔርንም ቃል ያልሰሙ፥ እነዚያ ሰልፈኞች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይሄዱ ነበር።


跟着我们:

广告


广告