Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሡ፥ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት ስፍራ አኑሩአቸው ብለህ እዘዛቸው አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እንዲሁም ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ልክ ካህናቱ ከቆሙበት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋይ አንሥተው በመሸከም ከእናንተ ጋራ እንዲሻገሩና ዛሬ በምታድሩበት ቦታ እንዲያኖሯቸው ንገራቸው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እንዲህም ብለህ እዘዛቸው፦ ‘በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሡ፤ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት ስፍራ አኑሩአቸው።’”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል፥ ካህናቱ ከቆሙበት ከዚያው ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ይዘው እንዲወጡ እዘዛቸው፤ ድንጋዮቹንም ወስደው ዛሬ ማታ በምትሰፍሩበት ስፍራ ያቆሙአቸው ዘንድ ንገር።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል የካ​ህ​ናት እግር ከቆ​መ​በት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ቀላል ድን​ጋ​ዮ​ችን እን​ዲ​ያ​ነሡ እዘ​ዛ​ቸው፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ውሰ​ዱ​አ​ቸው፤ ከዚ​ያም ሌሊት በም​ታ​ድ​ሩ​በት ቦታ በየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ጠብ​ቋ​ቸው።”

参见章节 复制




ኢያሱ 4:3
11 交叉引用  

ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።


መልሶም፦ እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ አላቸው።


ኢያሱም ለሕዝቡ፦ እነሆ፥ የተናገረንን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ሰምቶአልና ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፥ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል አላቸው።


እንዲህም ይሆናል፥ የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ ከላይ የሚወርደው የዮርዳኖስ ውኃ ይቋረጣል፥ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።


ኢያሱም ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእስራኤል ልጆች ያዘጋጃቸውን አሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ።


የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዘ አደረጉ፥ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንደ ተናገረው በእስራኤል ነገድ ቁጥር ከዮርዳኖስ መካከል አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ፥ በዚያም አኖሩአቸው።


ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፥ ስሙንም፦ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።


跟着我们:

广告


广告