Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 22:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ እግዚአብሔር በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአልና በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንታ የላችሁም ይሉአቸዋል ብለን ይህን አደረግን። በዚህም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን እግዚአብሔርን ከመፍራት ያስተዋቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፤ እግዚአብሔር ዮርዳኖስን በመካከላችን መለያ ድንበር ስላደረገው፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ድርሻ የላችሁም።’ ስለዚህ ዘሮቻችሁ፣ የእኛ ዘር እግዚአብሔርን እንዳይፈራ ሊያደርጉ ይችላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ ጌታ በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአልና በጌታ ዘንድ ድርሻ የላችሁም ይሉአቸዋል።’ በዚህም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን ጌታን እንዳይፈሩ ያደርጓቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እርሱ በእኛና በእናንተ፥ በሮቤልና በጋድ ሕዝቦች መካከል የዮርዳኖስን ወንዝ መለያ ድንበር አድርጎአል፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት አይኖራችሁም’ ይሉአቸው ይሆናል ብለን በመፍራት ብቻ ነው። በዚህም ዐይነት የእናንተ ዘሮች የእኛን ዘሮች ለእግዚአብሔር እንዳይሰግዱ ይከለክሉአቸው ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ዮር​ዳ​ኖ​ስን ድን​በር አድ​ር​ጎ​አ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላ​ች​ሁም ይሉ​አ​ቸ​ዋል፤ በዚ​ሁም ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከማ​ም​ለክ እን​ዳ​ያ​ወ​ጡ​አ​ቸው ብለን ይህን አደ​ረ​ግን።

参见章节 复制




ኢያሱ 22:25
13 交叉引用  

እንዲህም ሆነ፥ አንድ ብንያማዊ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የሚባል ምናምንቴ ሰው ነበረ፥ እርሱም፦ ከዳዊት ዘንድ እድል ፈንታ የለንም፥ ከእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ ብሎ ቀንደ መለከት ነፋ።


እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ “በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ! ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ! አሁን ቤትህን ተመልከት፤” ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደ ድንኳኖቻቸው ሄዱ።


ስለ በደለውና እስራኤልንም ስላሳተበት ስለ ኢዮርብዓም ኀጢአት እስራኤልን ይጥላል።”


እኔም መልሼ፦ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም እድል ፈንታና መብት፥ መታሰቢያም የላችሁም አልኋቸው።


ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም።


ይልቁንም ከልባችን ፍርሃት የተነሣ፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን አላችሁ?


ስለዚህም፦ መሠዊያ እንስራ አልን፥ ነገር ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት አይደለም፥


ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ፥ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻንን፦ በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንታ የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።


አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የእኔን የባሪያህን ቃል ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ፥ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አስነሥቶህ እንደ ሆነ፥ ቁርባንን ይቀበል፥ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ላይ እንዳልቀመጥ ዛሬ ጥለውኛልና በእግዚአብሔር ፊት ርጉማን ይሁኑ።


跟着我们:

广告


广告