Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 22:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር፥ የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር እርሱ አውቆታል፥ እስራኤልም ያውቀዋል፥ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደ ሆነ ዛሬ አታድነን፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ኀያሉ አምላክ፣ እግዚአብሔር! ኀያሉ አምላክ፣ እግዚአብሔር! እርሱ ያውቃል! እስራኤልም ይህን ይወቅ! ይህ የተደረገው በማመፅ ወይም ለእግዚአብሔር ባለመታዘዝ ከሆነ፣ ዛሬ አትማሩን!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “የአማልክት አምላክ ጌታ! የአማልክት አምላክ ጌታ! እርሱ አውቆታል፥ እስራኤልም ራሱ ይወቀው፤ በጌታ ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደሆነ ዛሬ አታድነን፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል እግዚአብሔር ነው! እርሱ የሁሉ ጌታ ነው! እርሱ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል አምላክ ነው! እኛ ስለምን ይህን እንደ ሠራን እርሱ ያውቃል፤ እናንተም ስለምን እንደ ሠራነው እንድታውቁት እንፈልጋለን፤ በእውነት ካመፅንና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት አጓድለን ከተገኘን፥ በሕይወት እንድንኖር አትፍቀዱልን፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ ነው፤ እርሱ ያው​ቃል። እስ​ራ​ኤ​ልም ያው​ቀ​ዋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ለበ​ደ​ልና ለመ​ካድ ከሆነ ዛሬ አያ​ድ​ነን፤

参见章节 复制




ኢያሱ 22:22
40 交叉引用  

ለአባቶቻችን በሰጠሃት ምድር ላይ በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ይፈሩህ ዘንድ፥ በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና፥ ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው።


ከዚህም በላይ በደለኛ እንዳልሆንሁ፥ ከእጅህም የሚያድን እንደሌለ አንተ ታውቃለህ።


የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፥ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።


ትከሻዬ ከመሠረትዋ ትውደቅ፥ ክንዴም ከመገናኛዋ ትሰበር።


ትዕቢት ባደረጉባቸው ነገር እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አሁን አወቅሁ አለ።


አንተ ግን፥ አቤቱ፥ አውቀኸኛል፥ አይተኸኛል፥ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፥ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፥ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።


እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።


ንጉሡም እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፥ ራሱንም ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ በአማልክት ሁሉ ላይ ራሱን ታላቅ ያደርጋል፥ በአማልክትም አምላክ ላይ በትዕቢት ይናገራል፥ ቍጣም እስኪፈጸም ድረስ ይከናወንለታል፥ የተወሰነው ይደረጋልና።


ንጉሡም ዳንኤልን፦ ይህን ምሥጢር ትገልጥ ዘንድ ተችሎሃልና በእውነት አምላካችሁ የአማልክት አምላክ፥ የነገሥታትም ጌታ፥ ምሥጢርም ገላጭ ነው ብሎ ተናገረው።


በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ።


ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ።


“ጠቦቶቼን ጠብቅ” አለው። ሦስተኛ ጊዜ፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ፦ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም፦ “በጎቼን አሰማራ።


ሲጸልዩም፦ “የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ፥ ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው አሉ።”


እንግዲህ በድዬ ወይም ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ እንደ ሆነ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ የሚከሱኝ ክስ ከንቱ እንደሆነ ግን ለእነርሱ አሳልፎ ይሰጠኝ ዘንድ ማንም አይችልም፤ ወደ ቄሳር ይግባኝ ብዬአለሁ” አለ።


ስለ ምን? ስለማልወዳችሁ ነውን? እግዚአብሔር ያውቃል።


ለዘላለም የተባረከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል።


እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን ሰዎችን እናስረዳለን ለእግዚአብሔር ግን የተገለጥን ነን፤ በሕሊናችሁም ደግሞ የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።


እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።


የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል አእላፋት አለቆች እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦


በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፥ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።


አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፥ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኩራት ነገር አይውጣ።


跟着我们:

广告


广告