ኢያሱ 2:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ቤትዋም በከተማ ቅጥር የተጠጋ ነበረና፥ እርስዋም በቅጥሩ ላይ ተቀምጣ ነበረና ከመስኮቱ በገመድ አወረደቻቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 መኖሪያ ቤቷ የከተማውን ቅጥር ተጠግቶ የተሠራ ስለ ነበር፣ ሰዎቹን በመስኮት አሾልካ በገመድ አወረደቻቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ቤትዋም የከተማውን ቅጥር ተጠግቶ የተሠራ ነበረና፥ እርሷም በቅጥሩ ውስጥ ተቀምጣ ነበር፤ እነርሱንም በመስኮቱ በኩል በገመድ አወረደቻቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ረዓብ የምትኖርበት ቤት ከከተማይቱ ቅጽር ግንብ ተጠግቶ በውስጥ በኩል የተሠራ ስለ ነበር ሰዎቹ በመስኮት በኩል ቊልቊል በተለቀቀ ገመድ ተንጠልጥለው ወደ ታች እንዲወርዱ አደረገች፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ቤቷም በከተማ ቅጥር የተጠጋ ነበረና፥ እርስዋም በቅጥሩ ላይ ተቀምጣ ነበርና በመስኮቱ በገመድ አወረደቻቸው። 参见章节 |