ኢያሱ 18:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፥ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን፦ ሂዱ፥ ምድሩንም ዞራችሁ ጻፉት፥ ወደ እኔም ተመለሱ፥ በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ ብሎ አዘዛቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ሰዎቹ የምድሪቱን ሁኔታ ለማጥናትና ለመመዝገብ ጕዞ ሲጀምሩ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ የምድሪቱን ሁኔታ አጥኑና በዝርዝር ከጻፋችሁ በኋላ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም እዚሁ ሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ እጥልላችኋለሁ” አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ሰዎቹም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ተመልክተው ሊጽፉ የሄዱትን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ሂዱ፥ ምድሩንም ዞራችሁ እዩና ጻፉት፥ ወደ እኔም ተመለሱ፤ በዚህም በሴሎ በጌታ ፊት ዕጣ እጥልላችኋለሁ።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ሰዎቹም የምድሪቱን ሁኔታ ለማጥናት ከመሄዳቸው በፊት ኢያሱ፥ “ወደ ምድሪቱ ሁሉ ሂዱ፤ አቀማመጥዋንም አጥንታችሁ መዝግቡ፤ ወደ እኔም ተመልሳችሁ ኑ፤ እኔም በዚህ በሴሎ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ዕጣ እጥልላችኋለሁ” የሚል መመሪያ ሰጣቸው፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን፥ “ሂዱ፤ ምድሩንም ዞራችሁ ጻፉት፤ ወደ እኔም ተመለሱ፤ በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ” ብሎ አዘዛቸው። 参见章节 |