ኢያሱ 18:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ድንበሩም ወደ ቤትሖግላ ወደ ሰሜን ወገን አለፈ፥ መውጫውም በዮርዳኖስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበረ፥ ይህ የደቡቡ ዳርቻ ነበረ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ከዚያም ሰሜናዊውን የቤትሖግላንን ተረተር ዐልፎ ይሄድና በስተ ደቡብ የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚገባበት እስከ ጨው ባሕር ወሽመጥ ይዘልቃል፤ ይህም ደቡባዊ ድንበሩ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ድንበሩም ወደ ቤትሖግላ ወደ ሰሜን ወገን አለፈ፤ የድንበሩም መጨረሻ በዮርዳኖስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበረ፤ ይህ የደቡቡ ዳርቻ ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ድንበሩ በቤትሆግላ ጐን ያልፋል፤ ከጨው ባሕር በስተሰሜን እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ደቡብ ድረስ ይሄዳል። ይህም የደቡቡ ድንበር ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 የድንበራቸውም ፍጻሜ በሰሜን በኩል ወደ ጨው ባሕር ልሳን ይደርሳል፤ በደቡብም በኩል ድንበራቸው ዮርዳኖስ ነው። ይህም በደቡብ በኩል ያለው ድንበር ነው። 参见章节 |