Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 18:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ሄደ፥ በቤትሖሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ዞረ፥ መውጫውም ቂርያትይዓሪም በምትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያትበኣል ነበረ፥ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በስተ ደቡብ ያለው ድንበር ከቤትሖሮን ትይዩ ካለው ኰረብታ ተነሥቶ፣ በምዕራብ በኩል ወደ ደቡብ በመታጠፍ፣ የይሁዳ ነገድ ከተማ ወደሆነችው ወደ ቂርያትበኣል ማለት ወደ ቂርያትይዓይሪም ያልፋል፤ ይህ እንግዲህ በምዕራብ በኩል ያለው ድንበር ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ሄደ፥ በቤትሖሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ዞረ፤ መጨረሻውም ቂርያት-ይዓሪም በምትባል በቂርያትበኣል በይሁዳ ልጆች ከተማ ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ይኸው ድንበር በሌላም አቅጣጫ ከዚህ ተራራ በስተ ምዕራብ ወደ ደቡብ በመታጠፍ የይሁዳ ነገድ ይዞታ ወደ ሆነችው ከተማ ወደ ቂርያትባዓል ወይም ቂርያትይዓሪም ያልፋል፤ ይህም በምዕራብ በኩል የሚገኘው ድንበር ነው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ድን​በ​ሩም ወደ ባሕር ሄደ፤ በቤ​ቶ​ሮ​ንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ አዜብ ዞረ፤ መው​ጫ​ውም ቂር​ያ​ታ​ርም በም​ት​ባል በይ​ሁዳ ልጆች ከተማ በቂ​ር​ያ​ት​በ​ኣል ነበረ፤ ይህ በባ​ሕር በኩል ነበረ።

参见章节 复制




ኢያሱ 18:14
9 交叉引用  

ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ በይሁዳ ካለች ከበኣል ተነሥተው በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።


ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያትበኣል፥ ረባት፥ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።


ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ፥ ቂርያትይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ደረሰ።


ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ አለፈ፥ ድንበሩም በታችኛው ቤትሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮትአዳር ወረደ።


የደቡብም ዳርቻ ከቂርያትይዓሪም መጨረሻ ነበረ፥ ድንበሩም በምዕራቡ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ወጣ።


የእስራኤልም ልጆች ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ፥ የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያትይዓሪም ነበረ።


ሁለተኛው ክፍል ወደ ቤት ሖሮን መንገድ ዞረ፥ ሦስተኛውም ክፍል በበረሃው አጠገብ ባለው ወደ ስቦይም ሸለቆ በሚመለከተው በዳርቻ መንገድ ዞረ።


跟着我们:

广告


广告