Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 15:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ፥ ቂርያትይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ደረሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም በመቀጠል ከተራራው ዐናት ተነሥቶ ወደ ኔፍቶ ምንጮች በማምራት፣ በዔፍሮን ተራራ ላይ ያሉትን ከተሞች ዐልፎ ይወጣና ቂርያትይዓይሪም ተብሎ ወደሚጠራው ወደ በኣላ ቍልቍል ይወርዳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚያም ድንበሩ ከተራራው ጫፍ ተነሥቶ ወደ ኔፍቶሐ ምንጮች ይደርሳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ይወጣል፤ ወደ ባዓላ ወይም ቂርያት ይዓሪም ይታጠፋል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ድን​በ​ሩም ከተ​ራ​ራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄ​ዳል፤ ወደ ዔፍ​ሮ​ንም ተራራ ይደ​ር​ሳል፤ ወደ ኢያ​ሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደ​ር​ሳል።

参见章节 复制




ኢያሱ 15:9
8 交叉引用  

ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ በይሁዳ ካለች ከበኣል ተነሥተው በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።


ዳዊትም እስራኤልም ሁሉ በኪሩቤል ላይ የተቀመጠውን ስሙም በእርሱ የተጠራውን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ያወጡ ዘንድ በይሁዳ ወዳለችው ቂርያትይዓሪም ወደ ተባለች ወደ በኣላ ሄዱ።


በኣላ፥ ዒዪም፥ ዓጼም፥ ኤልቶላድ፥


ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያትበኣል፥ ረባት፥ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።


የደቡብም ዳርቻ ከቂርያትይዓሪም መጨረሻ ነበረ፥ ድንበሩም በምዕራቡ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ወጣ።


የእስራኤልም ልጆች ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ፥ የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያትይዓሪም ነበረ።


ወጥተውም በይሁዳ ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፥ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፥ እነሆም፥ ከቂርያትይዓሪም በስተ ኋላ ነው።


በቂርያትይዓሪምም ወደ ተቀመጡት ሰዎች መልክተኞች ልከው፦ ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰዋል፥ ወርዳችሁም ወደ እናንተ አውጡት አሉ።


跟着我们:

广告


广告