Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 13:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእስራኤል ልጆች ግን ጌሹራውያንንና ማዕካታውያንን አላወጡም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሹርና ማዕካት በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ነገር ግን እስራኤላውያን የጌሹርንና የማዕካትን ሕዝብ ስላላስወጡ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በመካከላቸው ይኖራሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የእስራኤል ልጆች ግን ጌሹራውያንንና ማዕካታውያንን አላስወጡም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሹርና ማዕካት በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ይሁን እንጂ እስራኤላውያን የገሹርንና የማዕካን ሕዝብ አላስወጡም፤ ነገር ግን እነርሱ እስከ አሁን በእስራኤላውያን መካከል ይኖራሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን ጌሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ንን፥ መከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ን​ንና ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሴ​ሪና መከጢ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ይኖ​ራሉ።

参见章节 复制




ኢያሱ 13:13
13 交叉引用  

እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት እስራኤልም ሰማ።


የአሞን ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደተጠሉ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከሶርያውያን ከቤትሮዖብና ከሱባ ሀያ ሺህ እግረኞች፥ ከመዓካ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎች፥ ከጦብም አሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ቀጠሩ።


ሁለተኛውም የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረች ከአቢግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ።


የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚወጋ ነገር ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል።


የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ የአርጎብን ምድር ሁሉ ወሰደ፤ ይችንም የባሳንን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ በስሙ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ጠራ።


ሰልካን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ።


ገለዓድንም፥ የጌሹራውያንንና የማዕካታውያንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥


ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥ በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፥ እርሱም ከራፋይም የቀረ ነበረ፥ እነዚህንም ሙሴ መታቸው አወጣቸውም።


ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አልሰጠም፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የቀረበው በእሳት የተደረገ መሥዋዕት ርስታቸው ነው፥ እርሱ እንደ ተናገራቸው።


ዳዊትና ሰዎቹም ወጥተው በጌሹራውያንና በጌርዛውያን በአማሌቃውያንም ላይ ዘመቱ፥ እነዚህም እስከ ሱር እስከ ግብጽ ምድር ድረስ ባለው አገር ድሮውኑ ተቀምጠው ነበር።


跟着我们:

广告


广告