Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 11:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ ፈጽመውም አጠፉአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም አላስቀሩም፥ አሶርንም በእሳት አቃጠላት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እስትንፋስ ካለው ፍጡር አንድ እንኳ ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ፤ ራሷን አሦርንም በእሳት አቃጠሏት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ ፈጽመውም አጠፉአቸው፤ እስትንፋስ ያለውንም አላስቀሩም፤ አሦርንም በእሳት አቃጠላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እስራኤላውያን በሐጾር የተገኘውን ሰው ሁሉ ስለ ገደሉ በሕይወት የተረፈ አልነበረም፤ ከተማይቱም በእሳት ተቃጠለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ሰዎች ሁሉ በሰ​ይፍ ገደሉ፤ እስ​ት​ን​ፋስ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ሳያ​ስ​ቀሩ ሁሉ​ንም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ አሶ​ር​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ላት፤

参见章节 复制




ኢያሱ 11:11
6 交叉引用  

ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ከሚሰጥህ ከእነዚህ አሕዛብ ከተሞች ምንም ነፍስ አታድንም።


ከብቶቹን ሁሉ የከተሞቹንም ምርኮ ለእኛ በዘበዝን።


አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸው በመታሃቸውም ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፥ አትማራቸውም፤


እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ተራራማውን አገር ደቡቡንም ቈላውንም ቁልቁለቱንም ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ መታ፥ ማንንም አላስቀረም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።


ከተማይቱንም በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፥ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አደረጉት።


跟着我们:

广告


广告