ኢያሱ 10:37 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)37 እርስዋንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ሁሉ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፥ በኦዶላም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም፥ እርስዋንም በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም37 ከተማዪቱንም ከንጉሧ፣ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጋራ ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በዔግሎን እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)37 ያዙአትም፤ እርሷንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ሁሉ በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፤ በዔግሎም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም፤ እርሷንም በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም37 እርስዋንም ይዘው ንጉሡን፥ በከተማይቱና በአካባቢዋም የገጠር ከተሞች ያገኙትን ሁሉ ገደሉ፤ ኢያሱም ልክ በዔግሎን ባደረገው ዐይነት ከተማይቱ እንድትደመሰስ ፈረደባት፤ በእርስዋም ውስጥ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)37 እርስዋንም፥ ንጉሥዋንም፥ ከተሞችዋንም ሁሉ፥ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፤ በአዶላም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም ፤ እርስዋንም፥ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። 参见章节 |