Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 10:30 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እግዚአብሔርም እርስዋንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ እርስዋንም በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መታ፥ በእርስዋም አንዱን ስንኳ አላስቀረም፥ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረገው በልብና ንጉሥ አደረገ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እንዲሁም እግዚአብሔር ከተማዪቱንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። ኢያሱ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ፤ አንድም ሰው አላስተረፈም። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም በልብና ንጉሥ ላይ ደገመው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ጌታም እርሷንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፤ እርሷንም በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት መታ፥ በእርሷም አንድም እንኳ አላስቀረም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ ላይ እንዳደረገው እንዲሁ በልብና ንጉሥ ላይ አደረገ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እግዚአብሔርም በርስዋና በንጉሥዋ በእስራኤል ላይ ለእስራኤላውያን ድልን ሰጣቸው፤ ኢያሱም ከተማይቱንና በእርስዋ ያሉትን ሰዎች አጠፋ፤ በንጉሥዋም ላይ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ እንዳደረገው አደረገበት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋ​ንና ንጉ​ሥ​ዋን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እር​ስ​ዋ​ንም በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መታ፤ በእ​ር​ስ​ዋም አን​ዱን ስንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው በል​ብና ንጉሥ አደ​ረገ።

参见章节 复制




ኢያሱ 10:30
12 交叉引用  

ኢዩም ከአክዓብ ቤት የቀረውን ሁሉ፥ ታላላቆቹንም ሁሉ፥ ወዳጆቹንና ካህናቱን ማንም ሳይቀር በኢይዝራኤል ገደላቸው።


ከዚያ በኋላ ትመለሳላችሁ፥ በእግዚአብሔርም ፊት በእስራኤል ዘንድ ንጹሐን ትሆናላችሁ፤ ይህች ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ርስት ትሆንላችኋለች።


አምላካችንም እግዚአብሔር እርሱን አሳልፎ ሰጠን፤ እርሱንም ልጆቹንም ሕዝቡንም ሁሉ መታን።


አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸው በመታሃቸውም ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፥ አትማራቸውም፤


በዚያም ቀን ኢያሱ መቄዳን ያዛት፥ እርስዋንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት መታ፥ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው፥ ከእነርሱም አንዱን ስንኳ አላስቀረም፥ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረገ በመቄዳ ንጉስ አደረገ።


ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከመቄዳ ወደ ልብና አለፉ፥ ልብናንም ወጉ።


ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከልብና ወደ ለኪሶ አለፉ፥ ከበቡአትም፥ ወጉአትም።


የእግዚአብሔርም ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ ያዘ፥ በሰይፍም ስለት መታቸው፥ ፈጽሞም አጠፋቸው።


የዓድራ ንጉሥ፥ የልብና ንጉሥ፥ የዓዶላም ንጉሥ፥


እንዲህም ሆነ፥ እስራኤልን ሊያሳድዱ ሄደው የነበሩትን የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ ከገደሉአቸው በኋላ፥ እነርሱም በሰይፍ ስለት እስኪያልቁ ድረስ ከወደቁ በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ፥ በሰይፍም ስለት መቱአት።


የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው፥ ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ሬሳውንም ከዛፍ አወረዱት፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ጣሉት፥ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት።


የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥


跟着我们:

广告


广告