Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 10:26 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ከዚህም በኋላ መትተው ገደሉአቸው፥ በአምስቱም ዛፎች ላይ ሰቀሉአቸው፥ እስከ ማታም ድረስ በዛፎቹ ተሰቅለው ቈዩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከዚያም ኢያሱ ነገሥታቱን መትቶ ገደላቸው፤ በዐምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው፤ ሬሳቸውም እስኪመሽ ድረስ አልወረደም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ከዚህም በኋላ ኢያሱ መትቶ ገደላቸው፥ በአምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፎቹ ተሰቅለው ቈዩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከዚህም በኋላ ኢያሱ አምስቱን ነገሥታት ገድሎ በአምስት ዕንጨት ላይ ሰቀላቸው፤ ሬሳቸውም እስከ ምሽት ድረስ በዚያው ዋለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ከዚ​ህም በኋላ መት​ተው ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ በአ​ም​ስ​ቱም ዛፎች ላይ ሰቀ​ሉ​አ​ቸው፤ እስከ ማታም ደረስ በዛ​ፎቹ ላይ ተሰ​ቅ​ለው ቈዩ።

参见章节 复制




ኢያሱ 10:26
14 交叉引用  

ካሰበው ሰው ልጆች ሰባት ሰዎች አሳልፈህ ስጠንና ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ ለእግዚአብሔር እንሰቅላቸዋለን አሉት። ንጉሡም፦ እሰጣችኋለሁ አለ።


ለገባዖንም ሰዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት በተራራው ላይ ሰቀሉአቸው፥ ሰባቱም በአንድነት ወደቁ፥ እህል በሚታጨድበት ወራት በገብሱ መከር መጀመሪያ ተገደሉ።


ነገሩም ተመረመረ፥ እንዲህም ሆኖ ተገኘ፥ ሁለቱም በዛፍ ላይ ተሰቀሉ፥ ያም በንጉሡ ፊት በታሪክ መጽሐፍ ተጻፈ።


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የእግዚአብሔር የቍጣው ጽናት ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ በፀሐዩ ፊት ወደ እግዚአብሔር ስቀላቸው አለው።


ሕዝቡም ሁሉ መልሰው፦ ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን አሉ።


አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት።


በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤


የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው፥ ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ሬሳውንም ከዛፍ አወረዱት፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ጣሉት፥ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት።


ዛብሄልና ስልማናም፦ የሰው ኃይሉ እንደ ሰውነቱ ነውና አንተ ተነሥተህ ውደቅብን አሉት። ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደለ፥ በግመሎቻቸውም አንገት የነበሩትን ሥሉሴዎች ማረከ።


ሳሙኤልም፦ ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች አለ፥ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቆራረጠው።


跟着我们:

广告


广告