Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 10:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እስኪጠፉም ድረስ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች በታላቅ መምታት መምታታቸውን በፈጸሙ ጊዜ፥ ከእነርሱም ያመለጡት ወደ ተመሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ ኢያሱና እስራኤላውያን እስከ መጨረሻው ደመሰሷቸው፤ የተረፉት ጥቂቶቹ ግን ወደ ተመሸጉት ከተሞቻቸው ለመድረስ ቻሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እስኪጠፉም ድረስ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች በጽኑ ውግያ ድል ማድረጋቸውን በፈጸሙ ጊዜ፥ ከእነርሱም ያመለጡት ወደ ተመሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ጥቂቶች ብቻ አምልጠው ወደ የከተሞቻቸው ምሽጎች ገብተው ከሞት ለመትረፍ ቢችሉም እንኳ ኢያሱና የእስራኤል ሰዎች ሁሉንም ዐረዱአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ኢያ​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በታ​ላቅ መም​ታት መም​ታ​ታ​ቸ​ውን በፈ​ጸሙ ጊዜ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ያመ​ለ​ጡት ወደ ተመ​ሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥

参见章节 复制




ኢያሱ 10:20
12 交叉引用  

ዳዊትም አቢሳን፦ አሁን ከአቤሴሎም ይልቅ የሚጎዳን የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ ነው፥ እርሱ የተመሸጉትን ከተሞች አግኝቶ ከዓይናችን እንዳያመልጥ፥ አንተ የጌታህን ባሪያዎች ወስደህ አሳድደው አለው።


እነሆ፥ ክፉ ነገር አመጣብሃለሁ፤ ፈጽሞም እጠርግሃለሁ፤ ከአክዓብም በእስራኤል ዘንድ የታሰረውንና የተለቀቀውን ወንድ ሁሉ አጠፋለሁ፤


አብያና ሕዝቡ ታላቅ አመታት መቱአቸው፤ ከእስራኤልም አምስት መቶ ሺህ የተመረጡ ሰዎች ተገድለው ወደቁ።


በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩና፦ በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፥ ጮኻችሁም፦ ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ በሉ።


ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።።


ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ከሚሰጥህ ከእነዚህ አሕዛብ ከተሞች ምንም ነፍስ አታድንም።


እግዚአብሔርም በእስራኤል ፊት አስደነገጣቸው፥ በገባዖንም ታላቅ መምታት መታቸው፥ በቤትሖሮንም ዐቀበት በመንገድ አሳደዳቸው፥ እስከ ዓዜቃና እስከ መቄዳ ድረስ መታቸው።


እናንተ ግን አትዘግዩ፥ ጠላቶቻችሁንም አባርሩአቸው፥ በኋላም ያሉትን ግደሉ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሉአቸው አለ።


ሕዝብ ሁሉ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ በደኅና ተመለሱ፥ በእስራኤል ልጆች ላይ ምላሱን ማንቀሳቀስ የደፈረ ማንም ሰው የለም።


የእግዚአብሔርም ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ ያዘ፥ በሰይፍም ስለት መታቸው፥ ፈጽሞም አጠፋቸው።


እግዚአብሔርም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ መቱአቸውም፥ ወደ ታላቂቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴሮንም፥ በምሥራቅም በኩል ወዳለው ወደ ምጽጳ ሸለቆ አሳደዱአቸው፥ ማንንም ሳያስቀሩ መቱአቸው።


እንዲህም ሆነ፥ እስራኤልን ሊያሳድዱ ሄደው የነበሩትን የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ ከገደሉአቸው በኋላ፥ እነርሱም በሰይፍ ስለት እስኪያልቁ ድረስ ከወደቁ በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ፥ በሰይፍም ስለት መቱአት።


跟着我们:

广告


广告