Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 1:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በሁሉም ለሙሴ እንደ ታዘዝን እንዲሁ ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን፥ ብቻ አምላክህ እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ለሙሴ ሙሉ በሙሉ እንደ ታዘዝን ሁሉ፣ ለአንተም እንታዘዛለን፤ ብቻ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋራ እንደ ነበረ፣ አሁንም ከአንተ ጋራ ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በሁሉም ነገር ለሙሴ እንደ ታዘዝን እንዲሁ ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን፤ ብቻ ጌታ አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ለሙሴ ሁልጊዜ ስንታዘዝለት እንደ ነበረ ሁሉ፥ ለአንተም እንታዘዛለን፤ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ፥ ከአንተም ጋር ይሁን!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በሁ​ሉም ለሙሴ እንደ ታዘ​ዝን እን​ዲሁ ለአ​ንተ ደግሞ እን​ታ​ዘ​ዛ​ለን፤ ብቻ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።

参见章节 复制




ኢያሱ 1:17
19 交叉引用  

እኔም ባሪያህ፦ መልካሙንና ክፉውን ነገር ለመስማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኛል፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን አልሁ።


እግዚአብሔር ከጌታዬ ከንጉሥ ጋር እንደ ነበረ እንዲሁ ከሰሎሞን ጋር ይሁን! ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሡ ዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርግ!”


ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን “ጠንክር! አይዞህ! አድርገውም! አምላኬ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፤ አትደንግጥም፤ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነው ሥራ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እርሱ አይተውህም፤ አይጥልህምም።


እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ መንፈስ ያለበትን ሰው የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን በላዩ ጫንበት፤


የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲታዘዙት ከክብርህ አኑርበት።


የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።


ሙሴም እጆቹን ስለ ጫነበት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥበብን መንፈስ ተሞላ፤ የእስራኤልም ልጆች ታዘዙለት፥ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።


እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ እንሄዳለን።


በትእዛዝህ የሚያምፅ ሁሉ የምታዝዘውንም ቃል ሁሉ የማይሰማ፥ እርሱ ይገደል፥ ብቻ ጽና፥ አይዞህ።


በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፥ ከሙሴ ጋር እንደሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ አልጥልህም፥ አልተውህም።


በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነውና ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?


በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፥ ሙሴንም እንደ ፈሩ በዕድሜው ሁሉ ፈሩት።


ዳዊትም፦ ከአንበሳና ከድብ እጅ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያስጥለኛል አለ። ሳኦልም ዳዊትን፦ ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል አለው።


አባቴም በአንተ ላይ ክፋት ማድረግ ቢወድድ እኔም ባላስታውቅህ በደህና ትሄድ ዘንድ ባላሰናብትህ፥ እግዚአብሔር በዮናታን ይህን ያድርግ ይህንም ይጨምር፥ እግዚአብሔርም ከአባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።


跟着我们:

广告


广告