Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 8:48 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 አይሁድ መልሰው፦ “ሳምራዊ እንደ ሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በማለታችን እኛ መልካም እንል የለምን?” አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 አይሁድም መልሰው፣ “አንተ ሳምራዊ ነህ፤ ደግሞም ጋኔን ዐድሮብሃል ማለታችን ትክክል አይደለምን?” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 አይሁድ መልሰው “ሳምራዊ እንደሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በመናገራችን ትክክል አይደለንምን?” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 አይሁድ “አንተ ሳምራዊ ነህ፤ ጋኔንም አለብህ፤ ማለታችን ልክ አይደለምን?” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ ሳም​ራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔ​ንም እንደ አለ​ብህ መና​ገ​ራ​ችን በሚ​ገባ አይ​ደ​ለ​ምን?” ብለው ጠየ​ቁት።

参见章节 复制




ዮሐንስ 8:48
18 交叉引用  

የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ እግዚአብሔር፥ ሰዎች በሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው ለገዢዎች ባሪያ እንዲህ ይላል፦ ስለ ታማኙ ስለ እግዚአብሔር ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።


የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፥ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።


ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!


እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤


ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ ጋኔን አለበት አሉት።


ፈሪሳውያን ግን ሰምተው፦ ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ።


ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም።


እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ፦


አይሁድም፦ አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።


ከእነርሱም ብዙዎች፦ “ጋኔን አለበት አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ?” አሉ።


እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።


ስለዚህ ሳምራዊቲቱ፦ አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።


ሕዝቡ መለሱና፦ “ጋኔን አለብህ፤ ማን ሊገድልህ ይፈልጋል?” አሉት።


አይሁድም፦ “እኔ ወደ ምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም ማለቱ ራሱን ይገድላልን? እንጃ” አሉ።


አይሁድ፦ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም ስንኳ ሞተ ነቢያትም አንተም፦ ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አይቀምስም’ ትላለህ።


ክርስቶስ ራሱን ደስ አላሰኘምና፤ ነገር ግን፦ አንተን የነቀፉበት ነቀፋ ወደቀብኝ ተብሎ እንደ ተጻፈ ሆነበት።


እንግዲህ ነቀፌታውን እየተሸከምን ወደ እርሱ ወደ ሰፈሩ ውጭ እንውጣ፤


እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።


跟着我们:

广告


广告