Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 8:41 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እናንተ የአባታችሁን ሥራ ታደርጋላችሁ” አላቸው። “እኛስ ከዝሙት አልተወለድንም አንድ አባት አለን እርሱም እግዚአብሔር ነው” አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 እናንተ የምታደርጉት አባታችሁ የሚያደርገውን ነው።” እነርሱም፣ “እኛስ በዝሙት የተወለድን አይደለንም፤ አባታችንም አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው” ሲሉ መለሱለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 እናንተ የአባታችሁን ሥራ ትሠራላችሁ፤” አላቸው። እነርሱም “እኛስ ከዝሙት አልተወለድንም፤ አንድ አባት አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው፤” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 እንግዲህ እናንተ የምትሠሩት የአባታችሁን ሥራ ነው።” እነርሱም “እኛ በምንዝር የተወለድን ዲቃላዎች አይደለንም፤ አንድ አባት አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 እና​ንተ ግን የአ​ባ​ታ​ች​ሁን ሥራ ትሠ​ራ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “እኛ ከዝ​ሙት አል​ተ​ወ​ለ​ድ​ንም፤ ነገር ግን አንድ አባት አለን፤ እር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው” አሉት።

参见章节 复制




ዮሐንስ 8:41
17 交叉引用  

ፈርዖንንም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤል የበኩር ልጄ ነው፤


አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፥ አቤቱ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።


አሁን ግን፥ አቤቱ፥ እንተ አባታችን ነህ፥ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።


እኔ ግን፦ ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አደርግሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር የከበረችውን የአሕዛብን ሠራዊት ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።


በእውነት ኤፍሬም ለእኔ የከበረ ልጅ ነውን? ወይስ የተወደደ ሕፃን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አስበዋለሁ፥ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት ርኅራኄም እራራለታለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


እግዚአብሔር መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ሆሴዕን፦ ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለችና ሂድ፥ ጋለሞታን ሴትና የግልሙትናን ልጆች ለአንተ ውሰድ አለው።


እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።


እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።


እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ በአባታችሁ ዘንድ ያያችሁትን ታደርጋላችሁ።”


እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።


እናንተ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ እግዚአብሔር አንተን መርጦአልና ስለ ሞተው ሰው አካላችሁን አትንጩ፥ በዓይኖቻችሁም መካከል ራሳችሁን አትላጩ።


ደንቆሮ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ 2 ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? 2 የገዛህ አባትህ አይደለምን? 2 የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው።


ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።


跟着我们:

广告


广告