Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 8:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተም በግምጃ ቤት አጠገብ ይህን ነገር ተናገረ፤ ጊዜው ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቤተ መቅደሱ ግቢ፣ በግምጃ ቤት አጠገብ ሲያስተምር ነበር፤ ይሁን እንጂ ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር በግምጃ ቤት አጠገብ ይህንን ነገር ተናገረ፤ ጊዜው ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኢየሱስ ይህን ቃል የተናገረው በቤተ መቅደስ በገንዘብ መቀበያ ሣጥን አጠገብ ሆኖ ሲያስተምር ነው። ታዲያ፥ ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው በሙ​ዳየ ምጽ​ዋት አጠ​ገብ ይህን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ያ​ዙ​ትም፤ ጊዜው ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።

参见章节 复制




ዮሐንስ 8:20
17 交叉引用  

ከሌዋውያንም የነበሩ አራቱ የበረኞች አለቆች ዘወትር በሥራቸው ይቀመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ ነበሩ።


በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ፦ ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጕኦመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው፦ የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ።


ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበር፤ ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር፤


ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች፤


የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።


ዓይኑንም አንሥቶ መባቸውን በመዝገብ የሚጥሉ ባለ ጠጎችን አየ።


እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ።


ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።


አሁንም በበዓሉ እኩሌታ ኢየሱስ ወደ መቅደስ ወጥቶ ያስተምር ነበር።


ስለዚህ ሊይዙት ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም እጁን አልጫነበትም።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ ሊይዙት ወደዱ ነገር ግን እጁን ማንም አልጫነበትም።


እናንተ ወደዚህ በዓል ውጡ፤ እኔስ ጊዜዬ ገና ስላልተፈጸመ ወደዚህ በዓል ገና አልወጣም።”


ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር።


ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።


跟着我们:

广告


广告