Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 6:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ኢየሱስም እንጀራውን ያዘ፥ አመስግኖም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው እንዲሁም ከዓሣው በፈለጉት መጠን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ኢየሱስ ዐምስቱን እንጀራ አንሥቶ አመሰገነ፤ ለተቀመጡትም የሚፈልጉትን ያህል ዐደለ፤ ዓሣውንም እንዲሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ኢየሱስም እንጀራውን ያዘ፤ አመስግኖም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው፤ እንዲሁም ከዓሣው በፈለጉት መጠን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንጀራውን አንሥቶ ምስጋና ካቀረበ በኋላ ለተቀመጡት ሰዎች ዐደላቸው። እንዲሁም ዓሣዎቹን አከፋፈላቸው፤ ሁሉም የሚያስፈልጋቸውን ያኽል አገኙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን እን​ጀራ ይዞ አመ​ሰ​ገነ፤ ቈር​ሶም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሰጣ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች ሰጡ​አ​ቸው፤ ከዓ​ሣ​ውም እን​ዲሁ የፈ​ለ​ጉ​ትን ያህል ሰጡ​አ​ቸው።

参见章节 复制




ዮሐንስ 6:11
13 交叉引用  

ሰባቱንም እንጀራ ዓሣውንም ይዞ አመሰገነ ቍኦርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።


ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤


ኢየሱስም፦ “አሁን ካጠመዳችሁት ዓሣ አምጡ” አላቸው።


ኢየሱስም መጣና እንጀራ አንሥቶ ሰጣቸው፥ እንዲሁም ዓሣውን።


ወደ ምድርም በወጡ ጊዜ ፍምና ዓሣ በላዩ ተቀምጦ እንጀራም አዩ።


ዳሩ ግን ሌሎች ጀልባዎች ጌታ የባረከውን እንጀራ ወደ በሉበት ስፍራ አጠገብ ከጥብርያዶስ መጡ።


አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነዚህን ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል? አለው።


ይህንም ብሎ እንጀራን ይዞ በሁሉ ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ ቈርሶም ይበላ ዘንድ ጀመረ።


ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል፤ የሚበላም እግዚአብሔርን ያመሰግናልና ለጌታ ብሎ ይበላል፤ የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም እግዚአብሔርንም ያመሰግናል።


እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።


ወደ ከተማይቱም በገባችሁ ጊዜ መሥዋዕቱን እርሱ የሚባርክ ስለ ሆነ እርሱ ሳይወጣ ሕዝቡ ምንም አይቀምሱምና፥ ከዚያም በኋላ የተጠሩት ይበላሉና ለመብላት ወደ ኮረብታው መስገጃ ሳይወጣ ታገኙታላችሁ፥ በዚህም ጊዜ ታገኙታላችሁና አሁን ውጡ አሉአቸው።


跟着我们:

广告


广告