Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 21:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎችም ብዙ ነገሮች አሉ፤ ሁሉም ነገር ቢጻፍ፣ ለተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ ዓለም በቂ ቦታ የሚኖረው አይመስለኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኢየሱስም ያደረገው ሌላ ብዙ ነገር አለ፤ ሁሉም አንድ በአንድ ቢጻፍ፥ እንደሚመስለኝ፥ ዓለም እራሱ የሚጻፉትን መጻሕፍት ለመያዝ ቦታ አይበቃውም ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮች ደግሞ አሉ። እኔ እንደሚመስለኝ እርሱ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ ቢጻፉ ኖሮ የሚጻፉትን መጻሕፍት ዓለም ራሱ መሸከም ባልቻለም ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ የሠ​ራ​ቸው ሌሎች ብዙ ሥራ​ዎች አሉ፤ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ቢጻፍ ግን የተ​ጻ​ፉ​ትን መጻ​ሕ​ፍት ዓለም ስን​ኳን ባል​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበር። ከዐ​ሥራ ሁለቱ ሐዋ​ር​ያት አንዱ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጅ ሐዋ​ር​ያው ዮሐ​ንስ ጌታ​ችን በሥጋ ወደ ሰማይ ባረገ በሠ​ላሳ ዓመት፥ ቄሳር ኔሮን በነ​ገሠ በሰ​ባት ዓመት በዮ​ና​ና​ው​ያን ቋንቋ ለኤ​ፌ​ሶን ሰዎች የጻ​ፈ​ፍው ወን​ጌል ተፈ​ጸመ። ምስ​ጋና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን። አሜን።

参见章节 复制




ዮሐንስ 21:25
12 交叉引用  

እነሆ፥ ይህ የመንገዱ ዳርቻ ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ያስተውል ዘንድ ማን ይችላል?


እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና።


እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤


እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፦ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።


ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ


ከዚህም ሁሉ በላይ፥ ልጄ ሆይ፥ ተግሣጽን ስማ፥ ብዙ መጻሕፍትን ማድረግ ፍጻሜ የለውም፥ እጅግም ምርምር ሰውነትን ያደክማል።


የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም ልኮ፦ አሞጽ፦ ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፥ እስራኤልም ከአገሩ ተማርኮ ይሄዳል ብሎአልና አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል ዐምፆብሃል፥ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም አለ።


ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ።


ያዩት ሰዎችም አጋንንት ላደሩበት ሰው የሆነውንና ስለ እሪያዎቹ ተረኩላቸው።


跟着我们:

广告


广告