Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 16:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሴት ቀኗ ደርሶ ስትወልድ ትጨነቃለች፤ ከተገላገለች በኋላ ግን፣ ሰው ወደ ዓለም ተወልዷልና ስለ ደስታዋ ጭንቋን ትረሳለች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና በደስታዋ ምክንያት መከራዋን ከቶውን አታስበውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሴት በምትወልድበት ጊዜ የምጥ ቀንዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ከወለደች በኋላ ግን በዓለም ላይ ሕፃን ስለ ተወለደ ከመደሰትዋ የተነሣ ጭንቀትዋን አታስታውሰውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሴት በም​ት​ወ​ል​ድ​በት ጊዜ ወራቷ ስለ ደረሰ ታዝ​ና​ለች፤ ነገር ግን ልጅ​ዋን ከወ​ለ​ደች በኋላ ስለ ደስ​ታዋ ከዚያ ወዲያ ምጥ​ዋን አታ​ስ​በ​ውም፤ በዓ​ለም ወንድ ልጅን ወል​ዳ​ለ​ችና።

参见章节 复制




ዮሐንስ 16:21
18 交叉引用  

ለሴቲቱም አለ፤ በፀነሰሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።


መከራህንም ትረሳለህ፥ እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ።


ይደነግጣሉ፥ ምጥና ሕማም ይይዛቸዋል፥ እንደምትወልድ ሴትም ያምጣሉ፥ አንዱም በሌላው ይደነቃል፥ ፊታቸውም የነበልባል ፊት ነው።


ስለዚህ ወገቤ ሕመም ተሞላ፥ እንደምትወልድ ሴት ምጥ ያዘኝ፥ ከሕመሜ የተነሣ አልሰማም፥ ከድንጋጤም የተነሣ አላይም።


ሳታምጥ ወለደች፥ ምጥም ሳያገኛት ወንድ ልጅን ወለደች።


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፥ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፥ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።


አሁንስ ለምን ትጮኺአለሽ? እንደምትወልድ ሴት ምጥ የደረሰብሽ፥ ንጉሥ ስለሌለሽ ነውን? ወይስ መካሪ ስለ ጠፋብሽ ነውን?


አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል ከቶም አያመልጡም።


跟着我们:

广告


广告