Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 14:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኢየሱስም አለው፦ “አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ ‘አብን አሳየን’ ትላለህ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አንተ ፊልጶስ! ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋራ ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል፤ እንዴትስ፣ ‘አብን አሳየን’ ትላለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኢየሱስም አለው “አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ ‘አብን አሳየን’ ትላለህ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ፊልጶስ ሆይ! ይህን ያኽል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ ታዲያ፥ አንተ ‘አብን አሳየን’ እንዴት ትላለህ?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ፊል​ጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን አብ​ሬ​አ​ችሁ ስኖር አታ​ወ​ቀ​ኝ​ምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት አብን አሳ​የን ትላ​ለህ?

参见章节 复制




ዮሐንስ 14:9
16 交叉引用  

አቢሜሌክም ይስሐቅን ጠራ እንዲህም አለው፦ እነሆ ሚስትህ ናት እንዴትስ እርስዋን፦ እኅቴ ናትአልህ? ይስሐቅም፦ በእርስዋ ምክንያት እንዳልሞት ብዬ ነው አለው።


አንቺስ፦ አልረከስሁም በአሊምንም አልተከተልሁም እንዴት ትያለሽ? በቈላ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ያደረግሽውንም እወቂ፥ በመንገድም ላይ እንደ ተለቀቀች እንደ ፈጣን ግመል ሆነሻል፥


እርሱም መልሶ፦ የማታምን ትውልድ ሆይ፥ እስከመቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት አላቸው።


እናንት ግብዞች፥ የምድሩንና የሰማዩን ፊት ልትመረምሩ ታውቃላችሁ፥ ነገር ግን ይህን ዘመን የማትመረምሩ እንዴት ነው?


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።


እኔና አብ አንድ ነን።”


እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል።


እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።


እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። አሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል” አለው።


እንግዲህ፦ “አባትህ ወዴት ነው?” አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ “እኔንም ወይም አባቴንም አታውቁም፤ እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር” አላቸው።


ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ የሚሰበክ ከሆነ ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ፦ ትንሣኤ ሙታን የለም እንዴት ይላሉ?


እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቍኦጠረውም፥


እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤


እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


跟着我们:

广告


广告