Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 13:27 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ቍራሽም ከተቀበለ በኋላ ያን ጊዜ ሰይጣን ገባበት። እንግዲህ ኢየሱስ፦ “የምታደርገውን ቶሎ ብለህ አድርግ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ይሁዳም ቍራሹን እንጀራ እንደ ተቀበለ ወዲያው ሰይጣን ገባበት። ኢየሱስም፣ “የምታደርገውን ቶሎ አድርግ” አለው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እርሱም ቁራሹን ከተቀበለ በኋላ ሰይጣን ገባበት። ኢየሱስም “የምታደርገውን ቶሎ ብለህ አድርግ፤” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ይሁዳ ጉርሻውን ከተቀበለ በኋላ ወዲያውኑ ሰይጣን ዐደረበት፤ ኢየሱስም ይሁዳን፥ “ለማድረግ ያሰብከውን ቶሎ ብለህ አድርግ!” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እን​ጀ​ራ​ው​ንም ከተ​ቀ​በለ በኋላ ወዲ​ያ​ውኑ በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደ​ረ​በት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ግ​ዲህ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ፈጥ​ነህ አድ​ርግ” አለው።

参见章节 复制




ዮሐንስ 13:27
16 交叉引用  

በቀትርም ጊዜ ኤልያስ “አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት አሳብ ይዞታል፤ ወይም ፈቀቅ ብሎአል፤ ወይም ወደ መንገድ ሄዶአል፤ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል፤” እያለ አላገጠባቸው።


አንድ ድርሻ ሁሉን እንዲያገኝ ከፀሐይ በታች በተደረገው ሁሉ ይህ ነገር ክፉ ነው፥ ደግሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች፥ በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ነው፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።


ለንጉሡም አለቃ ለአርዮክ መልሶ፦ የንጉሡ ትእዛዝ ስለ ምን ቸኰለ? አለው። አርዮክም ነገሩን ለዳንኤል አስታወቀው።


ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፥ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል። ለዚህ ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።


ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።


ወዲያውም ፈጥና ወደ ንጉሡ ገብታ፦ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን ልትሰጠኝ እወዳለሁ ብላ ለመነችው።


ሰይጣንም ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በሚባለው በይሁዳ ገባ፤


እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው አሳብ ካገባ በኋላ፥


ነገር ግን ከተቀመጡት ስለ ምን ይህን እንዳለው ማንም አላወቀም፤


ኢየሱስም፦ እኔ እናንትን አሥራ ሁለታችሁን የመረጥኋችሁ አይደለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው ብሎ መለሰላቸው።


ጴጥሮስም፦ “ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ?


跟着我们:

广告


广告